እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና
እግዚአብሔር ባልሽ ሊሆን ይፈልጋል
ይህ አባባል የማይመስል ይመስላል። በእርግጥ አምላካችን ዘላለማዊ ቅዱስ አምላክ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከእስራኤል እና ከዓለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ ይህን አባባል ብዙ ጊዜ ተጠቅሟል።
ሌሎች አማልክትን ስታገለግል እና ከእርሱ ስትርቅ፤ በወዳጁ ደጋግሞ የሚታለልን ታማኝ እና አፍቃሪ ባል በመሆን እግዚአብሔር እራሱን ይገልጿል። ይህም በብዙ ጊዜ እንዳሳዘነው በቃሉ እንመለከታልን፡- “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣ ስታታልሉኝ ኖራችኋል” (ኤርምያስ 3፡20)። ነገር ግን በማያልቀው ፍቅሩ፣ ወደ እሱ እንዲመለሱ ዳግም እድልን የሚሰጥ አምላክ ነው።
በ2ኛ ቆሮንቶስ 11:2 ላይ ጳውሎስ አንባቢዎቹን ከክርስቶስ ጋር ትዳር እንዲመሰርቱ ከተደረገላቸው "ንጹሕ ድንግል" ጋር አመሳስሏቸዋል።
በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ፣ በበጉ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስና በሙሽራው መካከል የሚካሄደውን የሰርግ ድግስ ይገልጻል። እነዚህ ሁሉ ምስላዊ አገላለጾች ኢየሱስ በእሱ ከሚያምን ሰው ጋር ሊመሠርተው የሚፈልገውን ልዩና የጠበቀ ግንኙነትን ያሳያሉ።
ይህ የፍጹም ፍቅር ነው! ሙሽራውን በጣም ስለሚወዳት ነፍሱን ለእርስዋ አሳልፎ ሰጠ፤ ሊቀድሳት እና ከኃጢአቷ ሊያነጻት እንደወደደ እንመለከታለን (ኤፌሶን 5፡25-27)።
የኢየሱስን “የፍቅር ጥሪ” ትቀበላለህ?
ስለ አገልግሎታችን መረጃ ለማግኘት GlobalRize.org እና እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት ይጎብኙን።
ስለዚህ እቅድ
"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org