እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ጋብቻ ክርስቶስ ለአማኞች ያለውን ፍቅር የሚያንጸባርቅ ነው።

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ ስላላቸው ሚና ጽፏል። በማጠቃለያው እያንዳንዱ ባል ሚስቱን እንደራሱ አድርጎ መውደድ አለበት፤ ሚስትም ባሏን በአክብሮት መገዛት አለባት። ይህን ለማድረግም ለመረዳትም ሁልጊዜ የሚቀል አይደለም። ይሁን እንጂ ይህ ስለ ጋብቻ ብቻ አይደለም፤ ስለ “ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያን የሚያመለክት “ምሥጢር” ነው (ኤፌሶን 5፡32)።

ጳውሎስ ባሎችን ከክርስቶስ ጋር ያወዳድራል፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወዳትና እንደሚንከባከብ ሚስቶቻቸውን መውደድ፣ መመገብ እና መንከባከብ ሲያሳይክርስቶስ ለአማኞች ያለውን ፍቅር የሚያንጸባርቅ ነው።

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ ስላላቸው ሚና ጽፏል። በማጠቃለያው እያንዳንዱ ባል ሚስቱን እንደራሱ አድርጎ መውደድ አለበት፤ ሚስትም ባሏን በአክብሮት መገዛት አለባት። ይህን ለማድረግም ለመረዳትም ሁልጊዜ የሚቀል አይደለም። ይሁን እንጂ ይህ ስለ ጋብቻ ብቻ አይደለም፤ ስለ “ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያን የሚያመለክት “ምሥጢር” ነው (ኤፌሶን 5፡32)።

ጳውሎስ ባሎችን ከክርስቶስ ጋር ያወዳድራል፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወዳትና እንደሚንከባከብ ሚስቶቻቸውን መውደድ፣ መመገብ እና መንከባከብ አለባቸው። ክርስቶስ ነፍሱንም ለእሷ አሳልፎ ሰጥትዋል። ይህ በእርግጥ ከፍተኛ የሕይወት ደረጃን ያሳያል! ከዚህም በላይ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ በመሆኑ ሊከበር ይገባዋል። በተመሳሳይም ሚስቶች ባሎቻቸውን ማክበርና በሁሉም ነገር እንደ "ራሳቸው" ለእነሱ መገዛት አለባቸው። በዚህ መንገድ ክርስቲያናዊ ትዳር በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን የማይታይ ግንኙነት መገለጫ ይሆናል።

ጋብቻ ቅዱስ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ያለውን ፍቅር የሚያሳይ ነጸብራቅ ነው፤ ለሌሎች ያለንን ፍቅር፣ ታማኝነት እና የራስን ጥቅም በመሰዋት የሚናሳይበት ነው።

ባለትዳር ከሆኑ ትዳርዎ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ለሌሎች ምን ያስተላልፋል?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org