የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ጋብቻ በእግዚአብሔር የተዘጋጀ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ምዕራፎች አምላክ ዕፅዋትን፣ እንስሳትንና በመጨረሻም ሰዎችን ጨምሮ ሰማያትንና ምድርን እንዴት እንደፈጠረ ይዘግባል። አዳም የተባለውን ሰው ብቻ ሳይሆን ለእሱ ‘ተስማሚ የሆነች ረዳትም’ ፈጠረ። አምላክ ሴትን ከአዳም የጐድን አጥንት ሰራት፤ ወደ አዳም ሚስቱ እንድትሆን አመጣት። አዳምና ሔዋን የተፈጠሩት እንደ ሁለት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያዎቹ ሰብአዊ ባልና ሚስት ሆነው ነው።

ስለዚህ ጋብቻ በተለያዩ ባህሎች ውስጥ በጊዜ ሂደት የተገነባ ማህበራዊ ተቋም ብቻ አይደለም። በተቃራኒው ከመጀመሪያው በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው። ይህ ጋብቻን ዓለም አቀፋዊ ያደርገዋል። በመሆኑም ጋብቻ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነው። ስለዚህ አማራጭ አይደለም፣ የእያንዳንዱ ኅብረተሰብ የማዕዘን ድንጋይ መሆን አለበት፤ ይህ ማለት እያንዳንዱ ግለሰብ ማግባት አለበት ማለት አይደለም- ስለዚህ ጒዳይ ወደበኋላ የበለጠ እንመለከታለን።

በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ ያስቀመጠውን ደረጃ የማያሟሉ በርካታ ትዳሮችን ይዘግባል። ሰዎች ኃጢአተኞችና ፍጹማን ባለመሆናቸው ትዳራቸውም በዚሁ ምክንያት የተጎዳ ነው። ከዚህ አንጻር አምላክ ጋብቻን በተመለከተ ምን እንደሚል በጥንቃቄ ማዳመጥና ለትዳር ያለውን ዓላማ ማወቃችን ይበልጥ አስፈላጊ ነው።

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ይህን የንባብ ዕቅድ ከእኛ ጋር ያንብቡ!

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org