እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና
የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ያለበት በጋብቻ ውስጥ ብቻ ነው።
የግብረ ሥጋ ግንኙነት ልንደሰትበት የቻልነው የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ይህ ስጦታ እንዲያብብ፣ እግዚአብሔር አንዳንድ ግልጽ የሆኑ ድንበሮችን ሰጥቶናል። የግብረ ሥጋ ግንኙነት በጋብቻ ውስጥ የሚጠበቅና የጠበቀም ግንኙነት ነው።፤ እራስን ለማስደሰት ሳይሆን ለትዳር ጓደኛዎ ያለዎትን ፍቅር ለመግለጽ ነው፤ እንዲያውም ሐዋርያው ጳውሎስ “ሚስት አካሏ የራሷ አይደለም፤ የባሏ ነው፤ እንዲሁም ባል አካሉ የራሱ አይደለም፣ የሚስቱ ነው” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡4)።
ከአንድ ሰው ጋር “አንድ ሥጋ መሆን” የግብረ ሥጋ ግንኙነት ብቻ አይደለም፤ በተጨማሪም ስለ ስሜታዊ ቅርርብ እና ደኅንነት እንዲሁም በእያንዳንዱ ጋብቻ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው የዕድሜ ልክ ታማኝነት ነው። ስለዚህ ከጋብቻ ውጭ የሚደረጉ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች ሁሉ የተከለከሉ ናቸው።
ሰውነታችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ስለሆነ በውስጡ እግዚአብሔርን ማክበር ይገባናል። ዝሙት ልንፈጽም አይገባም። ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ “ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን” (ዕብ. 13፡4) በማለት ይመክረናል።
እግዚአብሔርን ስለ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሰጠውን ሕግ ይጠብቃሉ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org