እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ያላመነ ወንድ ወይም ሴት ማግባት ይቻላልን?

መጽሐፍ ቅዱስ ማንን ማግባት እንዳለብን ወይም ወላጆችን በትዳር ጓደኛ ምርጫ ላይ ሐሳብ እንዲኖራቸው ወይም እንደሌለባቸው አይገልጽም። አምላክ አንዲትን ሴት የአንድ ሰው ሙሽራ አድርጎ የሾመባቸው አንዳንድ ምሳሌዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፣ እነዚህ ግን የተለዩ ናቸው። በአጠቃላይ፣ ለማግባት ወይም ላለማግባት፣ ማንን እንደሚያገቡ የመምረጥ ነፃነት አለዎት። እርግጥ ነው፣ የወደፊቱን የትዳር ጓደኛን ባህሪ በጥንቃቄ ማጤን እና በውበት ላይ ብቻ አለማተኮር በጣም ብልህነት ነው፥ ምክንያቱም ቀሪውን ሕይወትዎን ከዚህ ሰው ጋር ስለሚያሳልፉ ነው።

አንድ ዋና የሆነ ግልጽ ገደብ አለ። እንደ አማኝ፥ ያላመነን ማግባት የለበትም። ጳውሎስ “ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ እንዳንጠመድ” አስጠንቅቆናል።

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ጋብቻ በጣም የጠበቀ ግንኙነት ነው፣ ማለትም" ከአንድ ሰው ጋር አንድ መሆን" ማለት ነው። በሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለዎትን እምነት ካላካፈሉ ይህ በእውነቱ አይቻልም።

ቃሉ ከሚያዘን ውጪ የተሚመሰረት ጋብቻ ጠንካራ መሠረት የለውም፥ አድካሚና የሚያታክት አልፎም ከጌታ ጋር ያሎትን ህብርት ሊሸረሽር ይችላል።

ከእግዚአብሔር ጋር ያለዎት ግንኙነት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው?

ቀን 7ቀን 9

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org