እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

የትዳር ጓደኛዎ በጌታ የማያምኑ ከሆኑስ?

በትናንትናው ጥናት አንድ ክርስቲያን፤ አማኝ ያልሆነን ሰው ማግባት እንደሌለበት ተመልክተናል። ነገር ግን ከጋብቻ በኋላ አንደኛው የትዳር አጋር ወደ እምነት የሚመጣበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ይህ ሁኔታ የትዳር ግንኙነት ላይ ውጥረት ሊያስከትል እንደሚችል ጥርጥር የሌለው ቢሆንም፤ ጋብቻን ለመፍርስ ግን ምክያት ሊሆን አይችልም። ይልቁንም አማኙ ለትዳር አጋሩ ታማኝ በመሆንና፣ ጥሩ ክርስቲያናዊ ስነምግባር በማሳየት ያላመነው የትዳር አጋሩ ወደ እምነት የሚመጣበት ዕድል መኖሩን ማወቅ ይገባዋል።

ይሁን እንጂ በክርስቶስ ያመነ ሰው ሕይወቱ ይለወጣል፤ ለዚህም ነው ይህን ሂደት መጽሐፍ ቅዱስ 'ዳግመኛ መወለድ' ብሎ የሚጠራው። ይህ እምነት፤ በሰው ሕይወት ውስጥ ዋና የሆኑትን፤ ባህሪ እና ፍላጐት ላይ መልካም ተጽዕኖ ያለው ትልቅ ለውጥ ነው።

በመሆኑም፤ ሕይወት ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ያመኑታ ጌታ ኢየሱስ ነው! የትዳር ጓደኛዎ እምነትዎን የማይጋሩ ከሆነ፤ በሕይወትዎ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች የእግዚአብሔር ቃል “ነገር ግን የማያምነው ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡15) ይላል።

ጋብቻዎን ለማዳን ያመኑትን ጌታን መካድ አይገባም። ነገር ግን በጌታ ኢየሱስ ማመንዎ የትዳር መፍረስ ምክንያት ሲሆን ይህ በጣም ያሳዝናል። መፋታትን ጌታ ይጠላል፤ ነገር ግን፣ ያመኑትን ጌታን የሚያስክድ ሆኖ ሲገኝ መለያየት ግድ ሊሆን ይችላል።

ዳግመኛ ተወልደዋል? ይህ እንዴት ሕይወትዎን ለውጦታል?

ቀን 8ቀን 10

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org