እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

በአዲሱ ምድር ላይ ሰዎች አያገቡም

በኢየሱስ ዘመን ከነበሩት ሰዱቃውያን መካከል አንዳንዶቹ፣ አንዲት መበለት እንደገና ስድስት ጊዜ ማግባቷን በተመለከተ መላምታዊና አስገራሚ ጥያቄ ሊጠይቁ ወደ ኢየሱስ መጡ። ጥያቄያቸው በእውነቱ በዚህ ላይ አይደለም፤ ነገር ግን ሰዎች ከሙታን ይነሣሉ የሚለው ሐሳብ አስቂኝ ነው ብለው መከራከር ስለፈለጉ ነበር። ሆኖም ኢየሱስ በጣም የተሳሳቱ መሆናቸውን አስረድቷል። ሰዎች በእርግጥ ከሙታን ይነሣሉ፣ ነገር ግን ከእንግዲህ አያገቡም ወይም አይጋቡም ሲል ገልጿል።

ይህ የትዳር ጓደኛቸው በሞት ለተለዩአቸው ሰዎች ጠቃሚ ሀሳብ ነው፤ ምንም እንኳን ሀዘናቸው ሙሉ በሙሉ ባይድንም፣ አዲስ ጋብቻን የሚፈልጉብት ወይም በቀሪው ሕይወታቸው ሳያገቡ የመቆየት አቅም የሚቸግራቸው ጊዜ ሊመጣ ይችላል (ለምሳሌ ለኑሮአቸው በቂ ገቢ የሌላቸውን ባላቸው የሞቱባቸውን እናቶችን አስቡ)። መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት መበለት ወይም ባል የሞተባት ሴት እንደገና ለማግባት ነፃ እንደምትሆን በግልጽ ይናገራል። ይህ በአዲሱ ምድር ላይ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አያመጣም፤ አዲሱ ጋብቻ ለሟች ባለቤታቸው ወይም ለሚስታቸው ታማኝ አለመሆንን አያመለክትም፤ ሁለተኛ ጋብቻቸው ልክ እንደ መጀመሪያው ጋብቻ በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ነው!

በመጨረሻ ወደ እግዚአብሔር ክብር ሲገቡ ከሁለቱም የትዳር ጓደኛ ጋር አይጋቡም፤ ነገር ግን "በሰማይ እንደ መላእክት" ይሆናሉ። በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም (ማቴዎስ 22፡30) ።

ቀን 5ቀን 7

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org