እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ያገቡ ወይም ያላገቡ መሆን ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ግንኙነት ተጽዕኖ የለውም

ስለ ጋብቻ ብዙ በማወቅዎ ማግባት የእያንዳንዱ ክርስቲያን የመጨረሻ የሕይወት ግብ እንደሆነ እንዲሰማዎ ሊያደርግ ይችላል፤ ነገር ግን አይደለም።

በሚስዮናዊነት በጣም ፍሬያማ የነበረው ሐዋርያው ጳውሎስም አላገባም። ጳውሎስም ይህንንም እንደ በረከት እንጂ እንደ ኪሳራ አልቆጠረውም። ምክንያቱም ያላገባ መሆኑ ሚስቱን ከማስደሰት ወይም ቤተሰቡን ከማሟላት ይልቅ "በጌታ ነገር" ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲያተኩር እንዳስቻለው ገልጾልናል።

ለክርስቲያኖች ሁለት ክቡር አማራጮች አሉት፣ ያላገቡ ሆነው መኖር ወይም በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል በዕድሜ ልክ በጋብቻ መኖር።

“ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል” (ምሳሌ 18:22)።

“ያላገባም የተሻለ አደረገ” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡38)። ስለዚህ አለማግባትም ሆነ ማግባት በጸጋ የሆኑ ስጦታ ናቸው።

“ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ምኞቴ ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከእግዚአብሔር የተቀበለው የራሱ የሆነ ስጦታ አለው፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡7)።

ዋናው ልናተኩር የሚገባው የሕይወት መመሪያ አንዱ ይህ ነው፡- “ብቻ እያንዳንዱ ሰው ጌታ እንደ ወሰነለት፣ እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው በዚያው ይመላለስ” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፡17)።

ያላገቡ ነዎት ወይስ ባለትዳር? 'የጋብቻ ሁኔታዎ' ከአምላክ የተገኘ ስጦታ አድርገው ትመለከቱታል?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org