እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ትዳር በማህበራዊ ግንኙነታችን ላይ ተጽእኖ ያሳድራል።

ጋብቻ በዋናነት በባልና በሚስት መካከል የሚደረግ ቃል ኪዳን ነው፣ ነገር ግን ይህ ቃል ኪዳን ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነትም ይለውጣል። አንድ ልጅ ሲያድግ ወላጆቹ ለእሱ ተጠያቂ ናቸው፤ በመሆኑም እነሱን መታዘዝ እና ማክበር አለበት።

ነገር ግን ልጁ ሲያድግ እና ሲያገባ ከወላጆቹ ጋር ያለው ግንኙነት ይለወጣል፤ እርግጥ ነው፣ ቤተሰቡን ሊያከብራቸው ይገባል። አሁን ዋና ኃላፊነቱ ሚስቱ እንጂ ወላጆቹ አይደሉም። መጀመሪያ ሊወዳት፣ ሊጠብቃት እና ሊንከባከባት ይገባል።

የጋብቻ ትስስር ከማንኛውም ትስስር የበለጠ ጠንካራ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ “ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል በሚስቱም ይጣበቃል” (ዘፍጥረት 2፡24)።

ጋብቻ በህብረተሰቡ ውስጥ ጠቃሚ እንዲሆን፤ ባል እና ሚስት በሌሎች ሰዎች ፊት በይፋ ቃል ኪዳን መፈጸማቸው አስፈላጊ ነው። በዚህ መንገድ ሌሎች እንደ ባልና ሚስት እንዲመለከቷቸው እና በማህበራዊ መዋቅሮች ውስጥም ስፍራቸውን እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።

በባህልዎ ውስጥ ጋብቻ ምን አቋም አለው? ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳብ ጋር ይስማማል?

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org