እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?ናሙና

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ጋብቻ የዕድሜ ልክ የቃል ኪዳን ግንኙነት ነው።

ጋብቻ በባልና ሚስት መካከል ካለው “የንግድ ውል” የበለጠ ነው። የእግዚአብሔር ምስክር ያለበት እና በባልና ሚስት መካከል የሚኖር የዕድሜ ልክ ቃል ኪዳን ነው። አምላካችን በእያንዳንዱ ሠርግ ቃል ኪዳን ላይ ይገኛል! ኢየሱስ በቃሉ፤ ወንድና ሴት ሲጋቡ፤ እግዚአብሔር አንድነታቸው አጣማሪ እንደሆነ ተናግሯል። ''እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው'' (ማቴዎስ 19፡6 እና በማርቆስ 10፡9)። ይህ ትዳራችን ላይ ትልቅ ክብደት እንድንሰጠው ያደርገናል!

ጋብቻ ኪዳን እንጂ ውል አይደለም፣ ሊቀለበስ አይችልም ነው። ጋብቻ “ሁለታችንም በሕይወት እስከኖር ድረስ” እንዲቆይ የታሰበ ነው። ለዚህም ነው እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ያስጠነቀቃቸው፣ “ከወጣትነት ሚስታችሁም ጋር ያላችሁን ታማኝነት አታጓድሉ” (ሚልክያስ 2፡15)። በመሆኑም ባልና ሚስት በሰርጋቸው ሥነ ስርዓት ላይ ለገቡት ቃል ኪዳን ታማኝነታቸውን እግዚአብሔር በአትኩሮት ይመለከተዋል።

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች የጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን በቁም ነገር አይመለከቱትም፤ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ፍቺዎች ሲኖሩ፤ የአምላክ ዓላማ ግን ይህ እንዳልሆነ ግልጽ ነው! አምላክ በቀሪው በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለትዳር ጓደኛችን ታማኝ እንድንሆን ይመክረናል።

እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለውን አመለካከት ይጋራሉ?

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

እግዚአብሔር ስለትዳር ያለው ሃሳብ ምንድን ነው?

"ሰዎች በትዳር ላይ የተለያየ አመለካከት አላቸው። አንዳንዶች ኋላ ቀር ሀሳብ አድርገው ይመለከቱታል፤ ሌሎች ደግሞ ጥልቅ የሆነ የፍቅር ስሜት ነው ብለው ይገልጹታል፤ ሌሎች ደግሞ በትዳር ጓደኛቸው ታማኝ አለመሆን ወይም በወላጆቻቸው መፋታት ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ለትዳር ያላቸው አመለካከት መልካምነት የሌለው ይሆናል። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አስተያየቶች ወይም ልምምዶች በላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ ጋብቻ ብዙ የሚናገረው ነገር አለው። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ጋብቻ ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ መረዳት ትችላለህ።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org