ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት ካህን ነው።
ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት ካህን ነው።
“እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤
አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣
እግዚአብሔር ምሏል፤
እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።(መዝሙር 110:4 )
የመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ስለ መስዋዕትነት ብዙ ዝርዝር መመሪያዎችን ይዘዋል። እነዚህ መሥዋዕቶች የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተሰረይና ወደ እግዚአብሔር ቅድስና ለመግባት አስፈላጊ ነበሩ። አምላክ የእንስሳትን ደም እንደ ምትክ ተቀብሏል፤ እነዚህ እንስሳት የተሰዉት ቅጣቱን በሚገባቸው ሰዎች ምትክ ነበር።
ይሁን እንጂ ሕዝቡ በተደጋጋሚ ኃጢአት ስለሠሩ መሥዋዕቶች በተደጋጋሚ መቅረብ ነበረባቸው። እነዚህ መሥዋዕቶች ለኃጢአት ችግር የመጨረሻ መፍትሄ አላመጡም። እንዲያውም የመጨረሻውን መሥዋዕት የሚያመለክቱ ነበሩ።
አምላክ የሌዊን ነገድ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ሾሟቸው ነበር። ይሁን እንጂ በመዝሙር 110 ላይ" እንደ መልከ ጼዴቅ" ስለተባለ አንድ ካህን እናነባለን። ይህ መልከ ጼዴቅ የኖረው ሌዋውያን ካህናት ከመሾማቸው ከረጅም ጊዜ በፊት ማለትም በአብርሃም ዘመን ነበር። ስለ እሱ ብዙ የምናውቀው ነገር የለም።
ነገር ግን በዚህ መዝሙር ውስጥ እግዚአብሔር በቀኙ ተቀምጦ አሕዛብን የሚገዛ ሰው እንደ መልከ ጼዴቅ፣ ለዘለዓለም ካህን ይሆናል ብሎ ማለ። ለሰው ልጆች ኃጢአት የመጨረሻ መፍትሔ ሊሰጡ እንደማይችሉ እንደ ሌዋውያን ካህናት ሳይሆን፣ እሱ ‘የተለየ ካህን’ ይሆናል። የዕብራውያን መጽሐፍ ኢየሱስ ይህ ካህን ነው ብሎ ይከራከራል። እርሱ ኃጢአትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይሸከማል።
ነገ ይህን እንዴት እንዳከናወነ እናነባለን።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org