ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ አሁንም ካህን ሆኖ ይማልዳል።
“በእግዚአብሔር ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን፣ ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።” (ዕብራውያን 10:21-22)
ኢየሱስ የመጨረሻውን መሥዋዕት አቅርቧል። አሁን እርሱ በአባቱ ቀኝ እንደ ሊቀ ካህናችን ሆኖ በአምላክ እና በሰው ልጆች መካከል እንደ መካከለኛ ሆኖ ያገለግላል። እርሱ ስለ እኛ ይማልዳል፣ እናም ስለዚህ በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን። ምንም እንኳን እኛ ራሳችን ኃጢአተኞች ብንሆንም በኢየሱስ ውብ እና ጻድቃን ነን እናም በአብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝተናል። ኢየሱስ ስለ እኛ ስለሚማልድ ከእንግዲህ ማንም ሊፈርድብን አይችልም። ሰይጣንም ቢሆን።
ይህ ደግሞ ከኃጢአትና ከእምነት ድክመት ጋር ለሚታገል ማንኛውም ክርስቲያን ትልቅ ማጽናኛ ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ እንዳረጋገጠልን፣ “ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም።”(1ኛ ዮሐንስ 2፡1-2)
ጌታ ኢየሱስ በአባታችን በእግዚአብሔር ፊት የሚማልደን ብቻ ሳይሆን፤ እርሱ ራሱ በዚህ ምድር ላይ ኖሮ ተፈትንዋል፤ ድክመቶቻችንን እና ትግሎቻችንን ይረዳናል። ጌታ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ስለሆነ የሚረዳንን ጸጋ ለመቀበል በምንፈልግበት ጊዜ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ለመቅረብ እንችላለን።
እርሱ ሁሉን ቻይ እና መሐሪ ነው። ለልጆቹ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እና ለዘላለም በዚያ ይሆናል። ምንም ነገር ከእሱ ፍቅር ሊለየን አይችልም!
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org