ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ የተስፋው ነቢይ ነው።
“አምላክህ እግዚአብሔር ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ” ( ዘዳግም 18:15)።
በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ሰበኩ ነቢያትን እናነባለን። አንዳንድ ጊዜ ጌታ ማስተላለፍ ያለባቸውን አዲስ ሀሳብ ሲገልጽላቸው፤ በሌሎች በርካታ አጋጣሚዎች ደግሞ ነቢያት ቀደም ሲል በሰፊው ይታወቅ እንደነበረው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለሰዎች አስታውቀዋል፣ ለምሳሌ ወደ ጣዖት ሲመለሱ ወይም ምድሪቱ በማህበራዊ ኢፍትሃዊነት በተሞላች ጊዜ፣ እነዚህ ነቢያት እንደ መንፈሳዊ መሪ፣ ሕዝቡ ንስሐ እንዲገቡና ወደ ጌታ እንዲመለሱ አስጠንቅቀዋል። ነገር ግን ሕዝቡ በአብዛኛው ጊዜ መልዕክታቸውን አያስተውልም ነበር።
ከነቢያቶቹም አንዱ ሙሴ፣ የእግዚአብሔር ቃል አቀባይ ነበር። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ትእዛዙን በቀጥታ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው፣ ከሲና ተራራ እንደተናገረው፣ ሕዝቡ ግን እጅግ ፈርተው ሙሴን ወደ ተራራው ወጥቶ እግዚአብሔር የሚናገረውን ሰምቶ እንዲያስተላልፍላቸው ለመኑት፤ ሙሴም እንደዚሁ አደረገ።
ሙሴ በሕይወቱ መገባደጃ ላይ ለሕዝቡ አምላክ "እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል" ብሏቸው ነበር። ነቢዩ ኢሳይያስም ስለ" የጌታ አገልጋይ" የተናገረ ሲሆን "የጌታ የተወደደችውን ዓመት" እንደሚሰብክም ተናግሯል።
ጌታ ኢየሱስም የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም እያወጀ እና ይህ ሰው እሱ ራሱ እንደሆነ ተናግሯል።
የጌታ ኢየሱስ ዋና መልእክት ምን እንደሆነ ያውቃሉ?
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org