ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ በነቢይነቱ የመጣበትን ሥራ ፈጽሟል።
“ለእኔ ያለህ ፍቅር በእነርሱ እንዲሆን፣ እኔም በእነርሱ እንድሆን፣ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እንዲያውቁህም አደርጋለሁ” (ዮሐንስ 17፡26)።
አብዛኞቹ ሰዎች የጌታ ኢየሱስን መልእክት የእግዚአብሔር ቃል አድርገው አልተቀበሉትም ነበር፤ ነገር ግን የነቢይነት ተልዕኮውን ከመፈጸም አላገደውም! ጌታ ኢየሱስን ሕይወቱን እንደሚያስከፍለው ቢያውቅም ማስተማሩን ቀጠለ፣ ትምህርቱም ፍሬ አፈራ። የጌታ ኢየሱስን ቃል በልባቸው ተቀብለው እርሱ መሢሕ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አመኑ፤ እውነቱም ነጻ አወጣቸው። በዮሐንስ 17፡3 ላይ እንደምንመለከተው እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
ጌታ ኢየሱስ ስለ አምላክ እውነቱን ያስተማረው በቃል ብቻ አልነበረም፤ በምልክቶቹና በተአምራቱም አጸናው። ከዚህም በላይ እርሱ እውነትና ሕይወት ነበር (ዮሐ. 14፡6)። ሐዋርያው ዮሐንስ ሲመሰክር "ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን'' ( ዮሐንስ 1፡14)።
ጌታ ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያውቅ እናም እንዲታወቅ የማድረግ ሥልጣን ስላለው እርሱን ስማ!
የጌታ ኢየሱስን ቃል ለሕይወትዎ ጠቃሚ ነው ብለው፤ በቁም ነገር ይወስዱታል?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org