ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ ፍጹም ድንቅ ነው።
“የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፣ ጥበብና ብርታት፣ ክብርና ሞገስ፣ ምስጋናም፣ ሊቀበል ይገባዋል።” (ራዕይ 5:12 )
የጌታ ኢየሱስን ሶስት ዋና ‘ተግባራት’ ለማጥናት 10 ቀናት ፈጅቶብናል። እርሱ የመጨረሻው ነቢይ ፍጹም ካህን እና ሁሉን ቻይ ንጉሥ ነው። ሦስቱም ‘ተግባራት’ ወይም ‘ቢሮዎች’ በትንቢት የተነገሩት ጌታ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው፤ ፍጻሜያቸውን ያገኙት በምድራዊ አገልግሎቱና በኃጢያት ክፍያው ሞት ነው። ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥነቱ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መዳን ሲውሉ በተግባሩ ላይ ተመልክተናል።
ጌታ ኢየሱስ የሰው መልክ ከመያዙ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት፣ የነቢይ፣ የካህን እና የንጉሥ ሚናዎቹን በትንቢት ተነግሯል፣ እያንዳንዳቸውም ወደ መሲሑ ያመለክታሉ። እነዚህ ቢሮዎች በጌታ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱ እና በሞቱ ወቅት፣ የሰው ልጅ ሊረዳው ከሚችለው በላይ ተፈጽመዋል።
ጌታ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ዘላለማዊ መዳን፤ የእግዚአብሔርን እውነት ገልጦልናል፤ እንደ ሊቀ ካህናችን ማልዶልናል እና እንደ ሉዓላዊ ንጉሣችን ነግሶልናል።
የጌታ ኢየሱስን ሥራ ለማጥናት አሥር ቀናት በቂ አይደሉም። ጌታ ኢየሱስ ለልጆቹ ስላደረገው ሁሉ እናመስግነው፤
እግዚአብሔር አብን ጌታ ኢየሱስ ስለገለጠልን እናመሰግናለን።
በእውነት ስለመራኸን እናመሰግናለን።
የዘላለም ሕይወትን መንገድ ስላሳየን እናመሰግናለን።
ለኃጢአታችን መንጻት ስላደረግህ እናመሰግናለን።
የእኛ ጠበቃ እና አማላጅ ስለሆንህልን እናመሰግናለን።
ንጉሳችን እና ጌታችን ስለሆንህልን እናመሰግናለን።
ጌታ ኢየሱስ ሆይ በሥልጣንና በሥልጣናት ሁሉ ላይ ሥልጣን ስላለህ እናመሰግንሃለን።
እንደ ዋና ነቢይ፣ ፍፁም ካህን እና የነገስታት ንጉስ በመሆንህ እናመሰግንሃለን።
ክብር፣ ግርማ፣ ሥልጣንና ኃይል ለዘላለም ለአንተ ይሁን። አሜን።
ስለ አገልግሎታችን መረጃ ለማግኘት GlobalRize.org እና እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት ይጎብኙን።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org