የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ቀን {{ቀን}} ከ11

የጌታ ኢየሱስን ንጉሥነት አልተቀበሉትም፡፡

“ጲላጦስ፡- ንጉሣችሁን ልስቀልን? አላቸው፤ የካህናት አለቆችም ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም ብለው መለሱ” ( ዮሐንስ 19:15 )

በጌታ ኢየሱስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ በሮማውያን ጭቆና ሥር ነበሩ፤ የፖለቲካ ነፃነትና ነፃነትን አብዝተው የፈለጉበት ጊዜ ነበር። ጌታ ኢየሱስ ተሰሚነትን ባገኘ ጊዜ ሰዎች እሱ ተስፋ የተደረገበት መሲሕ እንደሆነ እና የዳዊትን ዙፋን እንደሚያድስ፣ ከሮማውያንን ጭቆና ነጻ እንደሚያወጣቸው፤ ሰላምና ብልጽግና እንደሚያመጣላቸው ተስፋ አድርገው ነበር።

አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሣ ብቻ በመገበ ጊዜ፤ ሕዝቡ መጥተው ሊያነግሡት አሰቡ (ዮሐ. 6፡15)። ጌታ ኢየሱስ ግን ገለል አለ።

ጌታም እንደተናገረው፣ መንግሥቱ ከዚህ ዓለም አልነበረም (ዮሐ. 18፡36)። አላማው (እስካሁን) ፖለቲካዊ መንግስት መመስረት ሳይሆን፤ መንፈሳዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግስት ነው።

ሰዎች ራሳቸውን ለአምላክ እንዲሰጡና እርሱን ጌታና ንጉሥ አድርገው እንዲቀበሉ ፈልጐ ነበር፣ ነገር ግን በጊዜው ሰዎቹ በምድራዊ መንግሥት አገዛዝ ሥር በጭቆናና ተስፋ በመቈረጥ ውስጥ ነበሩ፤ ጌታ ኢየሱስንም ትተውት ሄዱ፤ በሃይማኖት መሪዎቹ ተነሳስተው እንዲገደል ጠየቁት።

ጌታ ኢየሱስን እንደ ንጉስዎ ይቀበላሉ?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 8ቀን 10

ስለዚህ እቅድ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org