የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ቀን {{ቀን}} ከ11

ጌታ ኢየሱስ በካህንነቱ የመጣበትን ስራ ፈጽምዋል።

“እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት፣ ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቧልና” (ዕብራውያን 7:27 )።

ካህናት በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል መካከለኛ ነበሩ። በሕዝቡ ስም ይጸልዩና መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። ነገር ግን ትናንት እንዳየነው ለኃጢአት ችግር የመጨረሻ መፍትሄ ሳያገኙ በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረባቸው። ኢየሱስ ፍጹም የተለየ ካህን ነበር።

እርሱ ራሱን አሳልፎ ሰጠ! ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ እርሱን "የእግዚአብሔር በግ" ብሎ የሚጠራው -የተሠዋ ፍጹም በግ። እርሱ ሙሉ በሙሉ ኃጢአት የሌለበት በመሆኑ ለሰው ልጆች ኃጢአት እንጂ ለራሱ ኃጢአት መሞት አላስፈለገውም።

በሺዎች የሚቈጠሩ የእንስሳት ደም የሰዎችን ኃጢአት ሊያስወግድ አልቻሉም። እነዚህ እንስሳት ኢየሱስን የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ነበሩ። የእርሱ ሞት የሰው ልጆችን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ "ለዘለዓለም አንድ ጊዜ" በቂ ነበር።


ጌታ ኢየሱስ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነው ለምን እንደሆነ ጥያቄ ሊነሣ ይችላል። አምላክ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ሰው ለመሆን፣ ለመከራና ለመሞት ፈቃደኛ የሆነው ለምንድን ነው? መልሱ ይህ ነው፦ ስለማያልቀው ፍቅሩ ነው። አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሣ ልጁን ሰጥቷል - ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


በጣም አስፈላጊው ጥያቄ ኢየሱስ ስለ አንተ/አንቺ ሲል መሞቱን ትቀበላለህ ወይስ አትቀበለውም የሚለው ነው። ጌታ ኢየሱስ በመስዋዕትነቱ የሰው ልጆችን ሙሉ ኃጢአት በሞቱ ቢከፍልም፤ እርሱን አዳኝህና ጌታህ አርገህ ተቀብለህ በእርሱ ካመንክ ብቻ የኃጢአት ይቅርታ ትቀበላለህ።

ጌታ ኢየሱስን ታምናለህ?

ቀን 5ቀን 7

ስለዚህ እቅድ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org