የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ቀን {{ቀን}} ከ11

ጌታ ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት ንጉሥ ነው።

“ሕፃን ተወልዶልናል፤
ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።
ስሙም፣ ድንቅ መካር፣
ኀያል አምላክ፣
የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
ለመንግሥቱ ስፋት፣
ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤” ( ኢሳይያስ 9: 6-7 )

የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ነገሥታት ነበሯቸው፤ አንዳንዶቹ መልካም ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ክፉ ነገሥታት ነበሩ። ንጉሥ ዳዊት ግን የተለየ እና የእግዚአብሔርን ልብ የሚሻ ሰው ነበር። በእግዚአብሔር ቃል እንደምንመለከተው፤ ንጉሥ ዳዊት ጉድለቶች ቢኖሩትም፣ ኃጢአትን በሠራ ጊዜ፣ ወደ አምላኩ ተመልሶ ይቅርታን የሚጠይቅ ሰው ነበር። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት አክበሮ የሚመራውንም ህዝቡ እንዲሁ እንዲያደርጉ ይመክር ነበር።

ልጁ ሰሎሞን በነገስ ጊዜ፤ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት ቃል ኪዳን ገባለት፤ “ቤትህና መንግሥትህ በፊቴ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ ዙፋንህም እንደዚሁ ለዘላለም የጸና ይሆናል” (2 ሳሙኤል 7:16)።የነገሥታትና የታሪክ መጻሕፍት የንጉስ ዳዊት ትውልድ ለብዙ መቶ ዓመታት እንደነገሡ ያስረዳናል።

ነገር ግን በመጨረሻ የእስራኤል ሕዝብ በግዞት ተወስደው የራሳቸው ንጉሥ አልነበራቸውም። ከዘመናት በኋላ፤ እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ፤ በቤተልሔም ከዳዊት ዘር የሆነው ጌታ ኢየሱስ ተወለደ፤ መልአኩም ጌታ እግዚአብሔር የአባቱን የዳዊትን ዙፋን እንደሚሰጠውና ለመንግሥቱም ፍጻሜ እንደሌለው ተናገረ ( ሉቃስ 1፡32-33)።

የእስራኤል ህዝብ ሲጠብቁት የነበረው የመጨረሻው ንጉሥ፡ ጌታ ኢየሱስ አገዛዙ ከጠበቁት የተለየ ነበር። ስለዚህ ክፍል ነገ በተጨማሪ እንመለከታለን።

ቀን 7ቀን 9

ስለዚህ እቅድ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org