ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ ከሁሉ የላቀ ንጉሥ ነው።
"ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡- “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል" (ማቴዎስ 28:18)።
ጌታ ኢየሱስ በሰማይም በምድርም ባለስልጣን ነው። እግዚአብሔር አብ ከሁሉ የላቀ ክብርና ክብር ያለውን የዓለሙን ቦታ ሰጠው። መላእክትና ሥልጣናት፣ ኀይላትም ተገዝተውለታል (1ኛ ጴጥሮስ 3፡22)። ምንም እንኳን የጌታ ኢየሱስ ገዢነት በምድር ላይ ሙሉ በሙሉ ባይታይም፣ ጌታ ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ ነው።
በዛ ቀን ከአምላክ ክብር የራቁትን ሥልጣናትና ኃይላት ባጠፋ ጊዜ፤ ጠላቶቹንም ሁሉ ከእግሩ በታች ካስገዛ በኋላ፤ በአዲሱ ምድር ላይ ይነግሣል፤ የሰላምና የደስታ መንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
እስከዚያው ድረስ፣ ጌታ ኢየሱስ በዋነኝነት የሚነግሰው “ከሁኔታዎች በስተጀርባ” ነው። የጳውሎስ መልእክት ለሮሜ ሰዎች ያረጋግጥልናል፤ ‘’እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን’’ (ሮሜ 8፡28)። ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ ስለሚስሉ፤ ይህንን ሁል ግዜ ለመረዳት ቀላል አይደለም፡፡
ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ የገባውን የተስፋ ቃል እንደሚጠብቅና፤ ወሰን በሌለው ጥበቡና እውቀቱ ለእኛ እና ለአለም የሚበጀውን እንደሚያውቅ ማመን አለብን።
ጌታ ኢየሱስ ‘ከሁኔታ በስተጀርባ' ሁሉንም ነገር እየተቆጣጠረ መሆኑን ሲያውቁ፤ በታሪክ ውስጥ ጌታ ኢየሱስ እየሰራ መሆኑን መረዳት ይችላሉ?
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org