ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና
ጌታ ኢየሱስ አሁንም ነቢይ ነው።
“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” ( የሐዋርያት ሥራ 1:8)።
ጌታ ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ ከአርባ ቀናት በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። በአምላክ ቀኝ ተቀመጠ። ምድራዊ አገልግሎቱ ተጠናቀቀ። ይህ ማለት ግን ከእንግዲህ የመጨረሻው ነቢይ አይደለም ማለት አይደለም። ኢየሱስ ምድርን ለቆ ከመሄዱ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ እስከ ምድር ዳር ድረስ ምስክሮቹ እንደሚሆኑ ነግሯቸው ነበር። መንፈስ ቅዱስም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ተብሎ ይጠራል፣ ለዚህ ተግባርም ያስታጥቃቸዋል። ይህ በጴንጤቆስጤ ቀን ተፈጽሟል። መንፈስ ቅዱስ በብዛት ፈሰሰ እና ፈርተው በተዘጉ በሮች ጀርባ የተደበቁ ደቀ መዛሙርት አሁን ወንጌልን በግልጽ እና በኃይል ሰበኩ። በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች አማኞች ሆኑ።
ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ ብቻ መሆን ይችል ነበር። አሁን ግን ምስክሮቹ የእግዚአብሔርን ቃል በአንድ ጊዜ በመላው ዓለም ያሰራጫሉ። ወንጌልን በሚሰብኩበት ጊዜ በቃሉ እውነት በእነሱ በኩል የሚናገረው ጌታ ኢየሱስ ነው። እውነተኛውን ቃል በመላው ምድር የሚያውጁት ትሑት ወኪሎቹ ናቸው።
ክርስቲያን በመሆንዎ ቃሉን እንዲናገሩና ምስክር እንዲሆኑ ተጠርተዋል። ይህን ያደርጋሉ?
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org