የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።ናሙና

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ቀን {{ቀን}} ከ11

ጌታ ኢየሱስ የተገፋ ነቢይ ነበር።

ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀርበው፣ “ይህን ሁሉ ነገር የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ሥልጣንስ የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት'' (ማቴዎስ 21፡23)።

ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይሰብክ ነበር፤ ትምህርቱ ብዙ ሰዎችን በመሳቡ ምክንያት ሰዎች እርሱ በሥልጣን እንደሚናገር አስተውለው ነበር። ነገር ግን በተለይ ለጌታ ኢየሱስ ለቤተሰቡ እና የከተማው ነዋሪዎች እርሱን ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ አድርጎ መቀበል ከብዷቸው ነበር።.

ከሁሉም በላይ ከልጅነቱ ጀምሮ ያውቁት ነበርና፣ እንዴት እርሱ እራሱ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ፍጻሜ መሆኑን እና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እውነትን ማወጅ የሚችል፤ እንዲህ ያለውን ትልቅ ነገር የይገባኛል ጥያቄ ሊያቀርብ የቻለው?!

ከዚህም በላይ ጌታ ኢየሱስ ያስተማረው ትምህርት ብዙውን ጊዜ ለመረዳት ወይም ለመቀበልም አስቸጋሪ ነበር። ጌታ ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎቹን "ግብዞች" ብሎ በመጥራቱ ወይም ደቀ መዛሙርቱ እሱን ለመከተል ሲሉ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው፤ በተናገረበት ወቅት የተናገረው ሃሳብ ለመረዳት ቀላል አልነበርም ነበር።

የካህናት አለቆችና ጸሐፍት የራሳቸው ሥልጣን በጌታ ኢየሱስ ስብከት አደጋ ላይ እንደወደቀ ተሰምቷቸው ነበር (ይህም አያስደንቅም፣ ምክንያቱም" መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት የሚዘጉ ግብዞች" ብሎ ጠርቷቸዋል)። ጥላቻና እና ጥርጣሬ ስለነበራቸው የጌታ ኢየሱስን የማስተማር ሥልጣን አልተቀበሉትም ነበር። በመጨረሻም የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ በማለት፤ እውነትን በመናገሩ እንደ ተሳዳቢ በመቁጠር እንዲሞት ፈረዱበት።

የጌታ ኢየሱስን ትምህርት የመጨረሻው እውነት አርገው ይቀበላሉ?

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻው ነቢይ፣ ካህን እና ንጉስ ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልድ ሆኖ ከዘላለም ጀምሮ አለ። ኃጢአተኞችንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ወደ ምድር መጣ። የጌታችን ኢየሱስ በማዳን ሥራው ውስጥ በሦስት ዋና ማንነቶቹ፤ እርሱም የመጨረሻውና የዘላለም ነቢይ፣ ካህን እና ንጉሥ መሆኑ ተገጿል። በዚህ የንባብ እቅድ ውስጥ እነዚህን ማንነቶቹን ለመረዳት 11 ቀናትን በመውሰድ እንመለከተዋለን።

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን GlobalRize ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ globalrize.org