የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

ድል አድራጊ ነኝ!

“በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን”ሮሜ 8፡37

ገና ውድድር ለማድረግ ስትገቡ፤አሸናፊዎች እንደምትሆኑ እርግጠኞች ሆናችሁ ስትገቡ እስቲ አስቡት፡፡ጥሩ ውድድር ለማድረግ ወይም አስገራሚ የሆነ ጨዋታ ለመጫወት ሣይሆን የጨዋታው ውጤት በመጨረሻ ወደ እናንተ እንደሚያደላ እርግጠኞች ሰትሆኑ፡፡

ማሊያችሁን ለብሳችሁ፤የጫማችሁን ማሰሪያ አጥብቃችሁ ሰውነታችሁን ስታሟሙቁ ውድድሩ ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም ከውድድሩ ሜዳ የምትወጡት ራሣችሁን እንደ አሸናፊዎች እየቆጠራችሁ ነው፡፡

የቡድን አባሎቶቻችሁን በተለየ መንገድ ነው የምትንከባከቧቸው?ሥህተት በሚፈፅሙበትስ ወቅት ልባችሁ ሳይቀየም ታልፏቸዋላችሁ?አሠልጣኞቻችሁ እርምትና መመሪያ በሚሰጧችሁ ወቅት ምላሻችሁ እንዴት ነው የሚሆነው? እንደምታሸንፉ እርግጠኞች ከሆናችሁ ተቀናቃኞቻችሁ ለሚወረውሩባችሁ የማይረቡ ንግግሮች ጆሮ ትሰጣላችሁ?

ጨዋታውን እንዳሸነፋችሁ ብታውቁ ሊኖራችሁ የሚችለውን በራስ የመተማመን መንፈስ አስቲ አስቡት፡፡

ወዳጆቼ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ሊኖረን የሚገባው አስተሳሰብ ይሄ ነው፡፡ኢየሱስ ውጊያውን ተዋግቶ በኃጢአትና በሞት ላይ የነበረውን ጦርነት ድል ነስቶቷል፡፡በእርሱ አማካይነት የተረጋገጠ ድል አለን፡፡ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ቢከበንም ወይም ሰዎች የሚፈልጉትን ቢያወሩም ከኢየሱስ የተነሣ ድል የእኛ ነው፡፡

ድል አድራጊው ንጉሱ ኢየሱስ በእርሱ አሸናፊዎች ስላደረገን ውጤት በማጣት፣በማሳፈር ወይም በሀሰት አንሸነፍም፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡-ለልምምድ ወይም ለውድድር በምትሄዱበት ወቅት አስተሳባችህ ምን እንደሚመስል አስተውሉ፡፡የምትገቡት በራስ መተማመን መንፈስ ነው ወይስ በፍርሃትና በጭንቀት ነው? በመጨረሻ ክርስቶስ ድልን እንደሚሰጥ ማስተዋል እንድትችሉ ትዝ ይላችሁ ዘንድ ምን እርምጃ ትወስዳላችሁ?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 10

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/