የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

በዓለም ውስጥ ብርሃን ነኝ

“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።”የማቴዎስ ወንጌል 5፡14

ጨለማ የብርሃን ተቃራኒ ሳይሆን የብርሃን አለመኖር መገለጫ ነው፡፡

የመጀመሪያው የዮሐንስ መልዕክት እግዚአብሔር ብርሃን እንደሆነና በእርሱ ውስጥ ጨለማ እንደሌለ ይናገራል፡፡(1ኛ ዮሐንስ 1፡5)ብርሃን ያሣያል፤ይገልጣል፤ይመራል እንዲሁም ሕይወትን ይሰጣል፡፡ጨለማ የሚነጨው ከኃጢአትና ነገሮችን ከመሸሸግ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ብርሃን በኢየሱስ አማካይነት ዓለማችንን ሞላው፡፡”ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።”(የዮሐንስ ወንጌል 3፡19) ኢየሱስ በውስጣችን ስለሚኖር ብርሃኑ በላያችን ላይ ያበራል፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 8፡13 ላይ ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” በማለት ተናግሯል፡፡

ኢየሱስ የዓለም ብርሃን እንደሆንን የተናገረው መንፈሱ በውስጣችን ከመኖሩ የተነሣ ነው፡፡ከመንፈሱ ጋር ጉዟችንን ስናደርግ ብርሃኑ በእኛ ላይ ያበራል፡፡ባትሪን የባትሪ ድንጋይ እንደሚያበራው ሁሉ እርሱ የእኛ የኃይል ምንጭ ነው፡፡

የኢየሱስ መንፈስ እርምጃችንን እንዲመራው ስንጠይቅ የብርሃኑ ኃይል ሥራውን እንዲጀምር እናደርገዋለን፡፡በምናደርገው እያንዳንዱ ምርጫ ላይ የኢየሱስ መንገድ ምርጥ መንገድ መሆኑን ስናምንናመታዘዛችን በተግባር ጭምር ሲገለፅየዚያን ጊዜ የብርሃኑ ኃይል ሥራ እንዲጀምር ምርጫችን አድርገነዋል ማለት ነው፡፡

ብርሃኑ የሚያበራው ዳኝነቱስለማያስደስተን አጫዋች ዳኛ መጥፎ ነገር ለመናገር እምቢ ስንል፤ለማሸነፍ ብለን መጥፎ ጨዋታ ሳንጫወት ስንቀርና የሕዝብ ትኩረት ለማግኘት ስንል በራስ ወዳድነት ስሜት ከመጫወት ይልቅ ሌላ ተጫዋች ከፍ ብሎ እንዲታይ ስናደርግ ነው፡፡

ከኢየሱሰ ጋር በምንኖርበት ወቅት በጨለማ ዓለም ወስጥ ብርሃን ሆነን እንታያለን፡፡

ኢየሱስ በውስጣችን ብርሃንን ይተው ዘንድ ወደ ሰማይ ተመልሶ ሄዷል፡፡ይሄንን ያደረገው ተመልካች የሆነው ዓለም በእኛ ውስጥ እርሱን ያይ ዘንድ ነው፡፡ብርሃን ኃይለኛ፤የሚፈውስ፤የሚሞቅና የሚስብ ነገር ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ሰዎች ወደ ብርሃን ይሳባሉ፡፡እኛ ወደ ምንጩ የምናሣይ፤በተራራ ላይ እንዳለ ብርሃን እንደሆንንኢየሱስ ይናገራል፡፡

ተግባራዊ እርምጃ ፡-ብርሃን መልካም ነገር ነው፡፡ሞትን ድል ነስቶ የተነሳው አዳኝ በእኛ ውስጥ ሲኖር ሕይወታችንን በበረከት ይሞላዋል፤ብርሃን እንዲያበራም ያደርገዋል፡፡የኃይል ምንጭ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነት አድርገን ስንኖር በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እርሱን በመገረም እስከሚመለከቱ ድረስ ሕይወታችን እንደ ኢየሱሰ ማብራት ይጀምራል፡፡

ቀን 8ቀን 10

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/