ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና
ነፃ ነኝ !
“ጌታ ግን መንፈስ ነው፤የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ” 2ተኛ ቆሮንቶስ 3፡17
አትሌቶች ብዙ ጫናዎች አሉባቸው፡፡አንዳንዶቹ ሌሎች ሰዎች ከእነርሱ ስለሚጠብቁት ነገር ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከራሣቸው የሚመነጩ ናቸው፡፡
ልጅ በነበርኩበት ወቅት አባቴ በስፖርት ውስጥ ተሣታፊ የነበረ ሲሆን ወንድሜ ደግሞ ደረጃ የነበረው አትሌት ነበር፡፡ሁለቱም ጥሩ አትሌቶች ስለነበሩ ለቤተሰቤ ሥም ክብርን ለማምጣት እኔም ጥሩ አትሌት መሆን አለብኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ይሄ ሃሣብ በሌላ ሰው የተነገረኝ ሣይሆን ከራሴ የመነጨ ነበር፡፡
ገምቱ እስቲ የምትመኟቸው ነገሮች በሙሉ በሕይወታችሁ ውስጥ እንደ ሠንሠለት ተያይዘው ሲመጡ፡፡ወንድሜ ጥሩ አትሌት ስለሆነ እኔም አትሌት መሆን አለብኝ፡፡ይሄኛውን ምኞቴን ያለፈው ዓመት አሳክቼዋለሁ በዚህኛው ዓመትም አሸናፊ እንደምሆን እጠበቃለሁ፡፡ነፃ ትምህርት አገኝ ይሆናል ወይም ደግሞ ድጋፍ የሚያደርጉልኝ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡በዚህ ወቅት በርትቼ ካልሰራሁ ነገሮችን ሁሉ ላጣ እችላለሁ፡፡
እያንዳንዱ ምኞታችሁ በትከሻችሁ ላይ እንደምትደርቡት የተያያዘ ሠንሠለት ነው የሚቆጠረው፡፡
እነዚህ ሁሉ የተያያዙ ምኞቶቻችሁ እያጎበጧችሁ ባሉበት ሁኔታ የችሎታችሁን ያህል በብቃት ለመወዳደር የምትችሉት እንዴት ነው?
ለክርስቶስ ተከታዮች እነዚህ ጫናዎች ሊጠፉ አይችሉም፡፡ነገር ግን ከእነዚህ ሸክሞች ነፃ ለመሆን እንችላለን፡፡ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታና እንደ ግል አዳኛችን በምንቀበልበት ወቅት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለናል፡፡በ2ተኛ ቆሮንቶስ 3፡17 ላይ እንደተፃፈው እርሱ ነፃነትን ይሰጠናል፡፡
በየዕለቱ በእርሱ ላይ በምንደገፍበት ወቅት ከእነዚያ እንደ ሠንሠለት ተያያዥነት ካላቸው ሸክሞቻችን ነፃ እያደረገን ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን ለውድድር እንድንቀርብ ያደርገናል፡፡
ነገር ግን ከእነርሱ ነፃ የተደረግን ቢሆንም ለእነዚያ ጫናዎች እስረኞች ሆነን መኖርን ልንለምድ እንችላለን፡፡በራሣችን ባህርይ ምክንያት የተጠመድን ሆነን እንኖራለን፡፡የዮሐንስ ወንጌል 3፡13 የሚነግረንና በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናገኘው መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን መሆኑን ነው፡፡
በእውነትና በእግዚአብሔር ማንነት ላይ ትኩረታችንን ባደረግን ቁጥር በእኛ ሁኔታ ላይ የሚኖረን ትኩረት እያነሰ ይሄዳል፡፡ይህ የምንጋፈጠውን ሸክም እንዲቀልል ያደርግልናል፡፡
ተግባራዊ ማድረግ፡-ዛሬ እያለፋችሁበት ያላችሁት ጫና ምንድነው?ውድድራችሁን በነፃነት ለማድረግ እንድትችሉ ከእነዚህ ሠንሠለቶች ነፃ ያደርጋችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ለምኑት፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/