የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

ነውር /ነቀፋ/ የሌለብኝ ሰው ነኝ፡፡

”እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።”ቆላስያስ 1፡22

በሻምፕዮንስ ሊግ የፍፃሜ ውድድር ላይ የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ለሁለተኛ ጊዜ ሥህተት በመሥራቱ ምክኒያት ጎል ሲቆጠርበት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጨዋታውን ይከታተሉ ነበር፡፡ሪል ማድሪድ 3 ለ1 በሆነ ውጤት አሸናፊ ለመሆን ቻለ፡፡ጨዋታውን የሚዘግበው ሰው የሊቨርፑሉን ግብ ጠባቂ በተመለከተ“ለሎሪስ ካርዩስ አስፈሪ ምሽት ነው”ብሎ ጮኸ፡፡ጥሩ አስተያየት አይመስልም፡፡

ከተናገራችሁ ወይም ድርጊቱን ከፈፀማችሁ በኋላ ያንን ጉዳይ ባሰባችሁት ጊዜ በፀፀት የምትሞሉበት ነገር ይኖር ይሆን?

ምናልባት ጨዋታ ላይ አጭበርብራችሁ ወይም ደግሞ ለዕድገታችሁ ስትሉ የቡድን አባላችሁን ጎድታችሁ ወይም ዋሽታችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ምናልባትም ለጨዋታው ፍፃሜ የተወሰኑ ሰከንዶች ቀርተው እያለ ባዶ መረብ ስታችሁ ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ በሻምፕዮን ጨዋታ ወቅት ሶስት ጎሎች በራሣችሁ ሥህተት ተቆጥሮባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ይሄ ደግሞ የቡድን አባላቶቹ በሙሉ ወይም አገራችሁ ተጠያቂዎች የሚያደርጓችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡

ምናልባት የትም ሥፍራ ብትሄዱ የፀፀት፤የሐዘንና የቁጭትን ሸክም ከላያችሁ ላይ ልታራግፉት አትችሉ ይሆናል፡፡

አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ ያ ነገር ሁሉ እንዳልተፈፀመ ቆጥሮ ነገሮችን ሁሉ በአዲስ መልክ እንጀምር ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ትላላችሁ?እንደ ጥፋተኛና ሥህተት አድራጊ ተደርጋችሁ አትቆጠሩም፡፡

በዚያ ፋንታ እናንተ ፍፁም ቅን እንደሆኑና ጥፋት እንደሌለባቸው ሰዎች የምትታዩ ትሆናላችሁ፡፡ ይህ ሰውዬ ከፍቅር የተነሣ ያደረጋችሁትንና ወደፊትም የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በራሱ ላይ ይሸከመዋል፡፡እናንተ እንደ ጥፋተኛና እንደ ሥህተተኛ እንዳትቆጠሩ በእናንተ ምትክ ሰው ጥፋተኛ በሰው ሁሉ ዘንድ ጥፋተኛ ለመባልና እናንተ ዘንድ ነፃ ትሆኑ እርሱ ወይም እርሷ ራሣቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡

ኢየሱስ የጥፋታችንን ዋጋ ለመክፈል ሲል ለእኔና ለእናንተ በመሥቀል ላይ ያከናወነው ይሄንን ነው፡፡እምነታችንንና መታመናችንን በእርሱ ላይ ስናደርግ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ይታደስ ዘንድ በመሥቀል ላይ ሞቶ የኃጢአታችንን ሸክም በላዩ ላይ አደረገ፡፡

በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበርነውን ሰዎች ለዘላለም የማዕዱ ተካፋዮች እንድንሆን ጋብዞናል፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው፤ሰው የሆነው፤ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት የኖረው፤ቅዱስና ሥህተት አልባ ስለሆነ ብቻ ነበር ኢየሱስ የኃጢአታችንን ሸክም መሸከም የቻለው፡፡

ኢየሱስ ስራችንን ስለ ሰራልን በራሳችን ብቃት ያለን ሰዎች እንደሆንን ለማረጋገጥ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ጥረት ማድረግ አይገባንም፡፡ ያለፈው ፤ የአሁኑና የወደፊቱ ሕይወታችን ምንም ይምሰል ከኢየሱስ ጋር ባለን ግንኙነት አዲስ ሕይወት ተሰጥቶናል፡፡እግዚአብሔር የሰራነውን ክፉ ድርጊት ሁሉ አያስበውም፡፡

ተግባራዊ እርምጃ ፡-እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንዳልሆናችሁ አድርጎ ስለሚቆጥራችሁ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስዳችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ጥቂት ደቂቃዎችን ወስዳችሁ ከሐፍረትና ከፀፀት እንዴት ነፃ ሊያድርጋችሁ እንደሚችል አሰላስሉ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 6ቀን 8

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/