የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

ፍፁም እንደሆነ ሰው እታያለሁ

“አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ቅዱሳን አድርጓቸዋልና” ዕብራውያን 10፡14

ከ1995 እስከ 2014/ እአአ/ ድረስ ለአጭር ጊዜ በቆየው የያንኪ ቅርጫት ኳስ አባል የነበረው ዴሬክ ጄተር “ከእናንተ በላይ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ነገር ግን እናንተ ከምትሰሩት በላይ የበለጠ እንዳይሰሩ የሚያቀርቡት ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡ይሄንን ነው የማምነው”ሲል ተነግሯል፡፡

በሕይወትና በስፖርት ውስጥ ወደ ፍፁምነት ደረጃ ለመድረስ መሥራት ይኖርብናል፡፡ይሄንን ግን ልንደርስበት የምንችለው ነገር አይደለም፡፡ትልቅ ችሎታና ትልቅ የሥራ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች እንኳን ወደ ፍፁምነት ደረጃ አይደርሱም፡፡ብዙ ርቀት ቢሄዱም ሊደርሱ ግን ፈፅሞ አይችሉም፡፡

በምንሰራው ስፖርት ውስጥ ጠንክረን የምንሰራ ቢሆንም ራሣችንን ከሌሎች ሰዎች ጋር ስናወዳድር ወይም ሌሎች ባስቀመጡልን መለኪያ ወይም ራሣችን ባስቀመጥነው መለኪያ አንፃር ስንመዝነው ዘወትር ውድቀት ያጋጥመናል፡፡ሆኖም እንደ አትሌቶች ብቁ ሆነን ለመገኘት ወደ ፍፁምነት ለመድረስ መጣር ይኖርብናል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ይህንን አስተሳሰብ ወደ ሌላው የሕይወታችን ክፍል በማዛወር ወደ መንግሥተ ሠማያት ለመግባት መሥራት እንደሚኖርብን እናስባለን፡፡ችግሩ በራሣችን ሥራ መግባት እንዳንችል እግዚአብሔር መንግሥተ ሠማያትን ለመውረስ ፍፁም መሆን አለባችሁ ይለናል፡፡

ለዚህ ነው እግዚአብሔር ሥራችንን የሰራው፡፡በመሥቀል ላይ ለእኛ የከፈለውን መሥዋዕት ስንቀበል ፍፁማን ያደርገናል፡፡እርሱ ብቻ ፍፁም በመሆኑ ፍፁማን ሊያደርገን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፡፡

እንደ አዳኝና ጌታ ኢየሱስን ስናምን በእግዚአብሔር ዓይን ፍፁማን እንሆናለን፡፡ሥራን መሥራት አይጠበቅብንም፡፡በእርሱ መታመን ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡የሚገርመው ነገር በእርሱ ላይ የመደገፍ ችሎታችን ሌላው ቀርቶ እምነታችን እንኳን ሣይቀር የሚመነጨው ከእርሱ ነው፡፡ሁሉንም ነገር ፈፅሞታል፡፡

በእምነታችን እያደግን ስንሄድ እግዚአብሔር ኢየሱስን እንድንመስል በማድረግ ወደ ፍፁምነት ይመራናል፡፡በዚች ምድር ላይ ወደ ፍፁምነት ባንደርስም እንኳን ወደ ሠማይ የምንደርሰው ፍፁማን ተደርገን ነው፡፡በእግዚአብሔር ፊት በምንቆምበት ወቅት ኃጢአታችንን ባስወገደው የኢየሱስ ፍፁም የሆነ መሥዋዕትነት በማመናችን ፍፁም እንደሆኑ ሰዎች እንቆጠራለን፡፡

“እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም፡፡”ቲቶ 3፡5

ተግባራዊ ማድረግ፡-ራሣችሁን ስለምታዩባቸው መንገዶች ወይም ሰዎች እናንተን ስለሚያዩበት የተወሰኑ መንገዶች በፅሑፍ አስፍሩ፡፡ ይህ እግዚአብሔር እናንተን ከሚያይበት ሁኔታ ጋር የሚጣጣም ነው?እግዚአብሔር እናንተን እንደ ፍፁማን እንደሚያያችሁ በየዕለቱ ራሣችሁን ለማሳሰብ ምን ታደርጋላችሁ?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 9ቀን 11

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/