ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና
አዲስ ፍጥረት ነኝ
“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፏል እነሆ ሁሉም አዲሰ ሆኗል”2ተኛ ቆሮንቶስ 5፡17
እቤታቸው ድረስ በመሄድ ዓይን ዓይናቸውን እያየ “ሕይወታችሁን እለውጠዋለሁ”እያለ ተጫዋቾችን የሚመለምል አንድ የኮሌጅ አሠልጣኝ ነበር፡፡
ይህ በራስ መተማመን የተሞላ ንግግር ነው፡፡
አንዳንድ አሠልጣኞች አሠልጣኞቻቸው ለመሆን እንዲችሉ ለአትሌቶች የማይሰጡት ተስፋ የለም፡፡ ነገር ግን ይሄኛው የተለየ ተስፋ ነው፡፡ይሄ አሠልጣኝ እያንዳንዳችን ያለንን ጥልቅ የሆነ የውስጥ ፍላጎት ግምት ውስጥ አስገብቶ ነው የተናገረው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ የማናስተውለው ሊሆን ቢችልም እነዚያ አትሌቶች በወቅቱ ባይገነዘቡትም ሁላችንም ብንሆን በሆነ ወቅት ላይ ሕይወታችን ወደተሻለ ሁኔታ እንዲለወጥ እንሻለን፡፡
ክርስቶስን ለመከተል በምንወስንበት ወቅት የተገባልን ቃል በትክክል ይህ ነው፡፡
2ተኛ ቆሮንቶስ 5፡17 “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፏል እነሆ ሁሉም አዲሰ ሆኗል” ይላል፡፡
ኢየሱስ ሕይወታችሁን ለመለወጥ ይፈልጋል፡፡ከእርሱ ጋር አዲስ የሆነ ግንኙነትን በመፍጠር አዲስ ፍጥረት እንድትሆኑ ይጋብዛችኋል፡፡
ራሣችሁን ሰጥታችሁ በስፖርት ዘርፍ መሣተፍ ከጀመራችሁበት ወቅት አንስቶ እንደ አትሌት ምን ለውጥ አምጥታችኋል?ይህንን ጉዞ ስትጀምሩ ከምትጫወቱት ጨዋታ ወይም ከውደድሩ አንፃር ለውጥ ልታደርጉ እንደሚገባችሁ ተገንዝባችሁ ነበር?
የምትፈልጉት ውጤት ላይ ለመድረስ መጀመሪያ በጀመራችሁበት ሁኔታ ላይ መቆም እንደማይገባችሁ ተገንዝባችኋል፡፡ማደግ ስለነበረባችሁ፡፡እንደዚህ ዓይነት ለውጥ በራሣችሁ ብቻ ልታደርጉ የምትችሉት አልነበረም፡፡ዕርዳታ ያስፈልጋችሁ ነበር፡፡
በእርግጥ በአግባቡ ሥራችሁን ብትሰሩም ነገር ግን አሰልጣኞቻችሁ፤ልምምድ የሚያሰሯችሁ ሰዎችና የቡድን አባሎቻችሁ ዛሬ ለምትገኙበት የአትሌትነት ደረጃ እንድትደርሱ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡በአንድ ወቅት የነበራችሁበት የአትሌትነት ደረጃ አዲስ በሆነ የአትሌትነት ደረጃ ተለውጧል፡፡
ይህ እንግዲህ ስፖርትን በሚመለከት ነው፡፡ከኢየሱስ ጋር የሚኖራችሁ ግንኙነት ዘለዓለማዊ የሆነ ተፅዕኖ አለው፡፡ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በራሳችሁ ጥረት አዲስ ፍጥረት ለመሆን አትችሉም፡፡ከጅምሩ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ተደርገን የተፈጠርን ቢሆንም ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር ጋር አለያይቶናል፡፡
ምሥጋና ለኢየሱስ ይድረሰውና ግንኙነታችን እንዲታደስ ተደርጓል፡፡ኢየሱስ ሕይወታችሁን ሊለውጥና አዲስ ፍጥረት ሊያደርጋችሁ ይፈልጋል፡፡ኢየሱስን ለመከተል ከመረጣችሁ ኢየሱስ በመሥቀል ላይ ስላከናወነው ነገር ምሥጋና ይድረሰውና ሙሉ በሙሉ ይቅር እንደተባላችሁ አውቃችሁ እረፉ፡፡በእናንተ የቀድሞ ማንነት ምትክ ይቅርታ የተደረገለት አዲስ ማንነት አለና፡፡
ተግባራዊ ማድረግ፡-ከኢየሱስ ጋር የግል ግንኙነት እንዲኖራችሁና አዲስ ፍጥረት ለመሆን ከፈለጋችሁ ከሚያገለግሏችሁ ጋር መነጋገር ወይም አሁኑኑ መጠነኛ ፀሎት ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ኃጢአተኞች ስለመሆናችሁና ይቅርታ የሚያስፈልጋችሁ መሆኑን እመኑ፡፡በሞተውና ከሙታን በተነሳው በልጁ በኢየሱስ እመኑና የሕይወታችሁ ጌታ ስለመሆኑ መስክሩ፡፡ቀደም ሲል ይህንን ግንኙነት ፈጥራችሁ ከሆነ ይህንን አዲስ ዕውቀት እንድትረዱትና ተግባራዊ እንድታደርጉት እግዚአብሔርን ጠይቁት፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/