የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

የመንፈስ ቅዱስ መኖሪያ ነኝ

“የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?”1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16

ክርስትና በዓለም ላይ ካሉ እምነቶች ሁሉ ያለው ትልቅ ልዩነት የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ ጋር ለመኖር ቃል መግባቱ ነው፡፡በየትኛውም ኃይማኖት ውስጥ አምላክ የሚባለው ራሱን ለተከታዮቹ አይሰጥም፡፡እግዚአብሔር ግን ከሥጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን ራሱን ሰጥቶናል፡፡

 እግዚአብሔር ሰዎች ከእርሱ ጋር ሕብረት እያደረጉ እንዲኖሩ ፈጥሯቸዋል፡፡አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን እስከበደሉበት እና ከእርሱ እስከ ተለዩበት ጊዜ ድረስ በዚያ ሕብረት ደስተኞች ነበሩ ፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ ይመላለስ በነበረበት ወቅት ደቀመዛሙርቱ በየዕለቱ ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ይችሉ ነበር፡፡በተሰቀለበት፤እንደገና በተነሳበትና እንደገና ተመልሶ ወደ ሰማይ እንደሚሄድ በነገራቸው ወቅት ምን ዓይነት የተዘበራረቀ ስሜት ተሰምቷቸው ይሆን?

እርሱ እንደገለፀላቸው ግን አፅናኙ ይመጣ ዘንድ እርሱ መሄድ ነበረበት፡፡

ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉት እኛ ከኢየሱሰ ጋር በአካል የመጓዝ ዕድሉ የለንም፡፡ሆኖም እነርሱም ቢሆኑ በየሰዓቱ ሁሉ ከእርሱ ጋር አልነበሩም፡፡ተስፋ የገባላቸውን መንፈስ ቅዱስን በላከበት ወቅት በውስጣቸው በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ተከታዮቹ ከእግዚአብሔር ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነት እንዲኖራቸው አስቻላቸው፡፡

በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር ህልውና የሚገለጠው በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲሆን በወቅቱ መንፈስ ቅዱስን የሚሞሉት ሰዎች ጥቂቶች ነበሩ፡፡ይሄም የሚሆነው ለተወሰነ ጊዜና ለተወሰነ ዓላማ ሲባል ነበር፡፡አሁን ግን የኢየሱስ መንፈስ እንደ ግል አዳኛቸው በሚቀበሉትና ድነትን ለማግኘት በእርሱ በሚያምኑት ሰዎች ልብ ውስጥ ይኖራል፡፡አሁን ቤቶቹ ነን;ቤተመቅደሱ ነን፡፡

ጳውሎስ በሮሜ ለሚገኙ አማኞች “አባ አባት ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና” በማለት ፅፏል፡፡ሮሜ 8፡15 እና 16

የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ የመኖሩ ጉዳይ ትምህርታዊ፤ሥነ መለኮታዊ አይደለም፡፡ልጆቹ ነን፡፡አባ የሚለው ቃል ከአራማይክ ቋንቋ የተመዘዘ ቃል ሲሆን አባትን ለመጥራት የሚውል ቃል ነው፡፡መንፈሱ በእኛ ውስጥ መኖሩ እውነትም የሚወደን ልጆቹ ስለመሆናችን ማረጋገጫ ነው፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡- ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችሁ ውስጥ የሚኖር ከሆነ ከፍጥረታት ሁሉ ታላቁን ሥጦታ ተቀብላችኋል፡፡እርሱን የሚያስደስት ሕይወት መኖር ትችሉ ዘንድ ጉልበት ይሰጣችኋል፤ብቸኛም አትሆኑም፡፡ሕይወታችሁን እንዲመራ መንፈስ ቅዱስን ትፍቅዱለታላችሁ?ፍጥረታትን የሚገዛው አምላክ በእናንተ ውስጥ መኖሩን ሌሎች ሰዎች እንዲያስተውሉ ያደርጋቸዋል?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/