የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

ፍፁም በሆነ ፍቅር የተወደድኩ ነኝ

“ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶሰ ጋር ሕይወትን ሰጠን፤በጸጋ ድናችኋልና”ኤፌ 2 ፡4- 5

ውጤት በምታመጡበት ወቅት፤አንድ ውድድርን በምታሸንፉበት ወይም ለፍፃሜ ውድድር በምትቀርቡበት ወቅት ሁሉም ሰው ይወዳችኋል ነገር ግን ኳስ ስትስቱ፤ውጤት አልመጣ ሲላችሁ፤ሥህተት ስትሰሩ ወይም ከውድድሩ ስትወጡ ምላሹ የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ሰዎች ድል የሚቀናቸውን ሰዎች የሚወዱት የክብራቸው ተካፋይ መሆን ስለሚፈልጉ ነው፡፡

እውነተኛ ፍቅር የሚለካው ግን በምላሹ አንድ ነገር የማይጠብቅ ከሆነ ነው፡፡በሕይወት የሌለ ሰው የሚሰጠው ነገር አይኖረውም፡፡ እግዚአብሔር የወደደን ሙታን በነበርንበት ወቅት ነው፡፡

ፍቅር የሚለካው በሚከፍለው ዋጋም ጭምር ነው፡፡ክርስቶስ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሣ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ክብሩን ካጣው በላይ ዋጋን ከፍሏል፡፡የወዳጆቹን ታማኝነትና ሕይወቱን ሣይቀር አጥቷል፡፡ኢየሱስ ሊጎዳው የሚችለውንና ከአባቱ ጋር የነበረውን ፍፁም የሆነ ግንኙነት ሲያጣም ታግሷል፡፡ ለእኛ ከነበረው ፍፁም ፍቅር የተነሣ ኢየሱስ ግርፋትን፣መጎዳትን፣ሥቃይን፣ውርደትን፣ሐፍረትን፣መናቅንና መገለልን ተቀብሏል፡፡ለእኛ ሲል እንዳልሆነ ሆኗል፡፡

እኛ ሕይወት ይሆንልን ዘንድ በሞት ውሰጥ አለፈ፡፡

እኛ ክብርን እንጎናፀፍ ዘንድ ውርደትን ተቀበለ፡፡

እኛ ነፃነትን እናገኝ ዘንድ ሥቃይን ተሸከመ፡፡

እኛ ወደ እግዚአብሔር የተጠጋን እንድንሆን እርሱ በመገለል ውስጥ አለፈ፡፡

እኛ ብቸኛ ሆነን እንዳንቀር በመተው ውስጥ አለፈ፡፡

ሰዎች ፍቅራቸውን የሚገልፁባቸው አንዳንድ መንገዶች መልካም ነገሮችን በማድረግ፤የማበረታቻ ቃላትን በመናገርና ልዩ የሆኑ ጊዜያትን በማሣለፍ ነው፡፡ኢየሱስ በመሥቀል ላይ በመሞት በዘመናት ተወዳዳሪ የሌለውን ታላቅ አገልግሎት ፈፅሟል፡፡ራሱን በሰጠበት ወቅት ታላቅ የሆነውን ሥጦታ ሰጠን፡፡በቃሉ ማለትም በመፅሐፍ ቅዱስ አማካይነት ታላቁን የማበረታቻ ቃል ሰጥቶናል፡፡ከእኛ ጋር እንደሚኖርና እንደማይተወንም ቃል በመግባት ልዩ የሆነ ጊዜን ሰጥቶናል፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡- -ኢየሱስ ፍፁም የሆነውን ፍቅር ስለሰጠን ልንፈራ አይገባም፡፡ከሰጠን ነገር በላይ ከእኛ የሚፈልገው ምንም ነገር የለም፡፡ኢየሱስ ፍፁም በሆነ ፍቅር ስለወደደን ለሌሎች ሰዎች ፍቅርን ለመሥጠት እንችላለን፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/