የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ

“ ልጆችም ስለሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።”ገላቲያ 4፡6,7

በአሜሪካ "የቫርሲቲ" ቡድን ውስጥ ለመሳተፍ ስለምትፈልጉ ብቻ በታችኛው የቫርሲቲ ቡድን ውስጥ ተሳትፋችሁ ታውቃላችሁ?አሠልጣኙ የበለጠ ጊዜ ከእናንተ ጋር እንዲወስድና ትኩረት እንዲሰጣችሁ፤እርሱ ወይም እርሷ ከሰዎች ጋር ግንኙነት በሚያደርጉበት መርሐ ግብር ላይ የተለየ ጊዜ እንዲሰጧችሁ ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ?

በአንድ ቡድን ውስጥ ያላችሁ እየመሰላችሁ ነገር ግን ቡድኑ ውስጥ በእርግጥ እንደሌላችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል?

በገላቲያ መልዕክት ውስጥ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑቱ ኢየሱስ በመሥቀል ላይ ካከናወነው መሥዋዕትነት የተነሣ ውስጠኛው ክፍል ውስጥ እንድንሆን ተደርገናል፡፡እግዚአብሔር ለልጆቹ የኢየሱስን መንፈስ ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለልጆቹ የኢየሱስን መንፈስ ነው የሚሰጣቸው፡፡

በልባችን ውስጥ በሚኖረው በመንፈሱ የእርሱ መሆናችንን እናውቃለን፡፡በውስጣችን ያለው መንፈስ ወደ አባቱ “አባ” በሚል ቃል (ትርጉሙ አባት ማለት ነው)እያለ ይጣራል፡፡ይሄ ሥም ቅርበትንና ፍቅርን የሚያመለክት ነው፡፡ውድ እንደሆኑ፤እንደሚፈቀሩና እንደሚወደዱ ልጆች እርሱ ንጉሥ ቢሆንም እንኳን ወደ አባት የመግቢያ መንገድን ከፍቶልናል፡፡

ማንም ሰው ቢሆን የሌላን ሰው ልጅ እንዲያሳድግ አንድን ሰው ሊያስገድደው አይችልም፡፡የሌሎች ሰዎች ልጆችን በማደጎ ለማሳደግ የወሰዱ ወዳጆቼና የቤተሰብ አባላቶቼ የሌላ ሰው ልጅን በማደጎ ለማሳደግ ብዙ ሂደቶችን አልፈዋል፡፡በአጋጣሚ የሚከናወን ነገር ሣይሆን በሚገባ ታስቦበት የሚከናወን የራሱ የሆነ ሥርዓት አለው፡፡

እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ስለሚቆጥረን እንደተመረጥን በዚህ እናውቃለን፡፡በቤተሰቡ ውስጥ በጠበቀ ግንኙነትና በፍቅር እንድንኖር ይፈልጋል፡፡አንድ ሰው በማደጎ ከተወሰደ በኋላ በተፈጥሮ ከተገኘው ልጅ እኩል መብት እንዲኖረው ከመደረግ ሌላ ምን የሚበልጥ ነገር ይኖራል?

የእግዚአብሔር ልጆች ሰለሆንን ወራሾችም ነን፡፡እንደ እግዚአብሔር ወራሾች የእግዚአብሔርን ክብር ለመውረስ ከኢየሱስ ጋር እንገናኛለን፡፡

በውስጥ ማንነታችሁ የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችሁ ሐሴት ታደርጋላችሁ?ከአባቱ ወይም ከአባቷ ጋር ለመሆን እንደሚናፍቁ ልጆች ከእርሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ትሻላችሁ?

ተግባራዊ እርምጃ ፡-እንደ እግዚአብሔር ልጆች ለእናንተ ስለተዘጋጀላችሁ ነገሮች ለጥቂት ጊዜ አስቡ፡፡በአሁኑ ወቅት በሕይወታችሁ ተግባራዊ ለማድረግ የምትፈልጉት ነገር የትኛውን ነው?

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/