የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን ማን ይለኛል?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ቀን {{ቀን}} ከ11

ተቀባይነት እና ዋጋ አለኝ!

“አቤቱ አንተ ኩላሊቴን ፈጥረሃልና፤በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛልና፤ግሩምና ደንቅ ሆኜ ተፈጥሬያለሁና አመሰግንሃለሁ”መዝሙረ ዳዊት 139፡ 13 እና 14

ፀሐፊው ዳዊት በመዝሙረ ዳዊት 139 ላይ ጥልቅ መሻታችንና ትልቁ ፍርሃታችን ከሆኑት ነገሮች አንዱን መርምሮ ያገኘዋል፡፡ ይህም በእውነት የምንታወቅ መሆናችን ፡፡

በቁጥር 1 ላይ “አቤቱ መረመርኸኝ አወቅኸኝም”ካለ በኋላ እግዚአብሔር በሕይወቱ ውስጥ ስላለው የማያቋርጥ ህልውናው ማብራራት ይጀምራል፡፡ዳዊት አንዲት ቃል ከመናገሩ አስቀድሞ እግዚአብሔር ያውቀዋል፡፡የዳዊት አዕምሮ ገና ሃሣብ ለማመንጨት እየፈለገ ባለበት ሁኔታ እግዚአብሔር ሃሣቡን ያውቀዋል፡፡

ወደየትም ሥፍራ ቢጓዝ የእግዚአብሔር መንፈስ በዚያ ሥፍራ ይገኛል፡፡ዳዊት ወደ ጥልቅ ውቅያኖስ ቢገባ እንኳን እግዚአብሔር በዚያም ሥፍራ ይገኛል፡፡

በዚህ መልክ መታወቅ አስፈሪ ነገር ነው፡፡አሠልጣኞቻችን ስለ ብርታቶቻችን ማለትም ለምሣሌ አዳዲስ ክህሎቶችን የምንገነዘብበትን ፍጥነት ወይም የቡድን አባሎቻችንን እንዴት እንደምናበረታታ እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን፡፡ነገር ግን አሠልጣኞቻችን ከዳኞች ጋር የምንጨቃጨቅ መሆናችንን ወይም በትላልቅ ጨዋታዎች ላይ ለመጫወት ያለብንን ችግር እንዲያውቁ አንፈልግም፡፡ሙሉ በመሉ የምንተዋወቅ ከሆነ የምንደብቀው ነገር አይኖርም፤ሥሀተቾቻችንንም ልንሸፋፍን አንችልም፡፡

ነገር ግን የወንጌል ውበት ይህ ነው፡፡ምንም እንኳን እግዚአብሔር እያንዳንዱን ኃጢአታችንን፤ሥህተቶቻችንንና የባህርይ ሕፀፆቻችን የሚመለከት ቢሆንም እኛን ከመውደዱ የተነሣ ከእርሱ ጋር እንታረቅ ዘንድ በእኛ ምትክ እንዲሞት ልጁን ላከልን፡፡

“የጋብቻ ምንነት”በተሰኘ ርዕስ በፃፉት መፅሐፍ ላይ ቲም ኬለር “እኛ ከምንገምተው በላይ ኃጢአተኞችና በሥህተት የተሞላን ስንሆን እኛ ተስፋ ከምናደርገው በላይ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት እጅግ የተወደድን ነን፡፡ወንጌሉ ይሄው ነው፡፡”ይላሉ፡፡

ሕይወት ከመዝራታችን በፊት እንኳን እግዚአብሔር ሥህተታችንን አውቆ ወዶናል፡፡እኛን ከጥንቃቄ ጋር ግሩም አድርጎ በራሱ አምሳል ከፈጠረን በኋላ እርሱን እንድናውቀውና ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር እንለማመድ ዘንድ መንገዱን ከፍቶልናል፡፡

እግዚአብሔር የእርሱን መልክና ክብሩን ታንፀባርቁ ዘንድ ልዩና ውብ አድርጎ ፈጥሯችኋል፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡-በዛሬው ዕለት በልባችሁ ያለውን ነገር ለጌታ እየነገራችሁትና በእናንተ ውስጥ መልካም ያልሆነውን ነገር እንዲገልጥላችሁ እየለመናችሁት ለተወሰነ ጊዜ በፀሎት ቆዩ፡፡ሥህተት እየፈፀማችሁ እንኳን ለማይቋረጠው ህልውናውና አቀባበሉ አመስግኑት፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር እኔን  ማን ይለኛል?

ዓለም፣አሠልጣኞቻሁ፣ወላጆቻችሁና አድናቂዎቻችሁ እናንተንና ሥራዎቻችሁን በሚመለከት ብዙ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ምን ይላል? ይህ ለ11ቀናት የተዘጋጀው ዕቅድ እናንተ የእርሱ ልጆች መሆናችሁን እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡ይህንን ሕይወት ለዋጭ የሆነውን ግንኙነት ይቅር የተባለና ድል አድራጊ የሚሉት ቃላት በአግባቡ ይገልፁታል፡፡በሁለንተናዊ መልኩ ሙሉ የሆነ አትሌት ለመሆን ትችሉ ዘንድ እነዚህን እውነታዎችን እንዴት ወደ ተግባር እንደምትለውጡት ለመማር ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያግዛችኋል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/