ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና
ሐሴት ማድረግ እችላለሁ
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርሰቶስ ሁሉን እችላለሁ”ፊሊጵስዩስ 4፡13
አትሌቶች ከሆናችሁ ፊሊጵስዩስ 4፡13ን ብዙ ጊዜ እንዳነበባችሁት እርግጠኛ ነኝ፡፡ይህንን ጥቅስ በከናቴራዎች ጀርባ ላይ፤በውኃ ጠርሙሶች ላይ፤በምትወዷቸው አትሌቶች የትዊተር ገፆች ላይ ታገኙታላችሁ፡፡ብዙ ጊዜ ይሄ ጥቅስ አትሌቶች ታላቅ ለመሆን ጥረት እንዲያደርጉ ለማነሳሳት ጥቅም ላይ የሚውል ጥቅስ ነው፡፡
በማራቶን ሩጫ ላይ ለመሣተፍ ትፈልጋለህ?“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርሰቶስ ሁሉን እችላለሁ”
የቅርጫት ኳስ ቡድንን መቀላቀል ትፈልጋለህ?“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርሰቶስ ሁሉን እችላለሁ”
የኦሎምፒከ ሜዳሊያን መሸለም ትፈልጋለህ?“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርሰቶስ ሁሉን እችላለሁ”
ሆኖም ይሄንን ጥቅስ ከአትሌቶች ስኬት አንፃር ብቻ የምታዩት ከሆነ በክርስቶስ ውስጥ ያለንን ኃይል እናጣዋለን፡፡
የፊሊጵስዩስ መልዕክት የፃፈው ጳውሎስ ሲሆን ወንጌልን በመስበኩ ምክኒያት እሥር ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ነበር የፃፈው፡፡ይህንን መልዕክት የፃፈው ለፊሊጵስዩስ አማኞች ሲሆን የሚቀርቡባቸውን ክሶችና ስደቶችን እንዲቋቋሙና ብርታትን ለማግኘት ወደ ክርስቶስ እንዲመለከቱ ለማበረታታት ነበር፡፡
እነዚህ ክርስቲያኖች የኢየሱስ ተከታዮቸ በመሆናቸው ብቻ ማቆሚያ በሌለው ማስፈራራት፤እሥርና በሞት ውስጥ ሣይቀር የሚያልፉ ሰዎች ነበሩ፡፡በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እያሉ ጳውሎስ ሐሴት እንዲያደርጉ ያበረታታቸዋል፡፡እግዚአብሔር ቅርባቸው በመሆኑ በፍርሃትና በጭንቀት ሣይወጠሩ የሚያዳምጣቸውና ሁኔታውን መቆጣጠር እንደሚችል የሚያውቁ በመሆኑ ጭንቀታቸውን ለእርሱ አሳልፈው ይሰጡታል፡፡
መፍራት በሚገባቸው ወቅት እንኳን እኛ ሥጋ ለባሾች ልንረዳ የማንችለውን ሠላም ይሰጣቸዋል፡፡
ጳውሎስ “ሁሉን ማድረግ እችላለሁ”ሲል ዘወትር በጌታ ደስ ስለመሰኘት እየተናገረ ነው፡፡ይሄ ጥቅስ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆን በእምነታቸው ፀንተው እንዲኖሩ፤በፍቅርና በቅድስና እንዲኖሩ አማኞችን የሚያበረታታበት የመዝጊያው ምክሩ ነው፡፡
በክርስቶስ ውስጥ ስንሆን ብርቱ ለመሆን የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ እንደሚኖሩን፤በመከራ ውስጥ ሐሴት ማድረግ እንዳለብንና ኃጢአትን መታገል እንዳለብን የሚያስተምረው ጳውሎስ ብቻ አይደለም፡፡ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ሲፅፍ
“የመለኮቱ ኃይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለሰጠን በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።”በማለት ይናገራል፡፡
በውስጣችን በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከእርሱ ጋር መራመድ እንችል ዘንድ እግዚአብሔር የምንፈልገውን ነገር ሁሉ በመስጠት በሕይወታችን ላይ ያለው ዓላማ እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡በእርሱ ውስጥ ዕውን የሆነና የተትረፈረፈ ሕይወት ለመኖር እንችል ዘንድ ሁሉንም ነገር ሰጥቶናል፡፡
ተግባራዊ እርምጃ ፡-እግዚአብሔር በአጠገባችን ሆኖ የሚያስፈልገንን ዕገዛ ሁሉ እንደሚያደርግልን በመገንዘብ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብትሆኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ወስዳችሁ ሐሴት አድርጉ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/