የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ዘለዓለማዊ የሆነ ዋስትና አለኝ

“እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።”1ኛ ዮሐንስ 5፡11-13

”የዘላለምን ሕይወት እንዳለኝ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?”

በጌታ ገና አዲስ በነበርኩበት ወቅት የጠየቅኩት ጥያቄ ነው፡፡እርግጠኛ ለመሆን የፈለግኩ ቢሆንም በሕይወቴ ውስጥ ያለውን ነገር ስለማውቅ በራሴ ላይ እምነት አጣሁ፡፡ከሌሎች ሰዎች የደበቅኩት ቢሆንም ኃጢአት እንዳለ ግን አውቄያለሁ፡፡

ክርስቲያኖች ይሄንን ነገር መፈፀም የለባቸውም፡፡አይደል?ዘወትር እንደ ክርስቲያን መኖር ካልቻልኩ እንደ ክርስቲያን ልቆጠር እችላለሁ?

ኢየሱስ ስለ ኃጢአቴ እንደሞተ አውቃለሁ፡፡አሁን ግን ሕጉን ለመከተል መበርታት ይኖርብኛል፡፡ልክ ነው አይደል?ችግሩ ግን ከአቅሜ በላይ ነበረ፡፡

ሆኖም ጥያቄዬ የተሳሰተ ነበር፡፡ዘለዓለማዊ ነገር የሚባለው የወደፊት ጉዳይ ሣይሆን የአሁን ነው፡፡በዮሐንስ ወንጌል 17፡3 ላይ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”የሚል ቃል እናገኛለን፡፡

እውነተኛው ሕይወት፤ከሞትን በኋላ የሚከናወን ነገር አይደለም፡፡ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኘው ኢየሱስን በማወቅ ነው፡፡”እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።"1ኛ ዮሐንስ 5፡11-12

በተመሳሳይ ሁኔታ ኢየሱስን የሚያስደስት ሕይወት ለመኖር የራሴ የሆነ አቅም የሌለኝ ሲሆን በራሴ ኃይል ለራሴ ይቅርታ ማድረግ አልችልም፡፡ሁሉንም መፈፀም ያለበት እርሱ ነው፡፡ሁለቱንም ነገሮች በበላይነት መምራት ይኖርበታል፡፡

ይህ ቢሆኖ ኖሮ ያንን የሚያክል ፀጋ ፈፅሞ አያስፈልገኝም ነበር፡፡ነገር ግን ነፃነት የሚሰጥ ነገር ነው፡፡

በመንፈሱ ውስጥ የእግዚአብሔር ልጅ በውስጣችን የሚኖር ከሆነ ሕይወት ይኖረናል፡፡ያ መንፈስ ይመራናል፤ኢየሱስን ለመታዘዝም ብርታትን ይሰጠናል፡፡የእኔ ደስታ ኢየሱስን ማወቅና መንፈሱ በእኔ ውስጥ ሥራውን ያከናውን ዘንድ ነው፡፡

ተግባራዊ እርምጃ ፡-ዮሐንስ ይህንን መልዕክት የፃፈው በኢየሱስ ለሚያምኑ ሰዎች ሲሆን ያሳሰባቸውም የዘለዓለም ሕይወት እንዳላቸው እንዲገነዘቡ ነበር፡፡ይሄንን ልንገነዘብ የምንችለው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ስለሚነግረን ነው፡፡የድነታችን እውነታ የሚለካው በስሜታችን ሣይሆን በእግዚአብሔር እውነተኛነት ላይ ነው፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/