ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና
ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ መገናኘት እችላለሁ
“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።”ዕብራውያን 4፡16
በአንድ ወቅት አንድ አሠልጣኝ የሚያሠለጥናቸው ተጫዋቾች ለእርሱ ግልፅ እንዳልሆኑለት አጫወተኝ፡፡ለምን ሊያነጋግሩት እንደማይመጡ እንዳልገባው ነገረኝ፡፡
“ዘወትር ግልፅ የሆነ ፖሊሲ እንዳለኝ እነግራቸዋለሁ…ይሄንን ስል ደግሞ ከልቤ ነው፡፡ወደ እኔ እንዲመጡ በጣም እፈልጋለሁ”አለኝ፡፡
“ነገሩ እኮ ቀላል ነው፡፡ስለሚፈሩህ ነው” ብዬ መለስኩለት፡፡
ፊቱ ላይ የብስጭት፤የመጎዳትና የመገለል ስሜት ተነበበበት፡፡ይሄ ንግግሩ አንድ አሠልጣኝ በሰዎች ለመቀረብ ቀላል መሆን እንደሚኖርበትና ይሄ ደግሞ ለምን እንደሚጠቅም በሠፊው እንድነጋገር በር ከፈተልን፡፡
ኢየሱስ ይህንን ምሣሌነት በአገልግሎቱ ጊዜ ሁሉ በተግባር አሳይቶታል፡፡በተለይ ለጉዳዩ አፅንዖት በመሥጠት በማቴዎስ ወንጌል 11፡28 ላይ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”በማለት ተናግሯል፡፡
እርግጥም ሸክም የነበረባቸው አሠልጣኙ የሚያሰለጥናቸው ተጫዋቾች ሠላም ማግኘት እንደማይችሉ ስላወቁት ወደ እርሱ መሄድ አልፈለጉም፡፡
የአሠልጣኙ ማንነት በምን መልኩ ማሸነፍ ብቻ ነው የሚኖርብን የሚል አስተሳሰብ ሰለነበረው ተጫዋቾቹ ከእርሱ ጋር መገናኘት ፈሩ፡፡በእያንዳንዱ ግንኙነት ወቅት ተጫዋቹ ማድረግ ስለነበረበትና ስላጎደለው ነገር ሠፊ ውይይት እንዲከፈት የሚደረግ ሲሆን ተጫዋቹ በግሉ ስላደረገው ጥረት ግን ምንም አይነገርም፡፡ከዚህ የተነሣ ከእርሱ ጋር በተገናኙ ቁጥር ሸክማቸው በየጊዜው እየከበደ መጣ፡፡
ያስከተለው ውጤት ግልፅ በተደረገው የፖሊሲ በር አለመግባት ሆኖ አረፈው፡፡
አሠልጣኙ ግን የሰጠሁትን ምክር በፀጋ ተቀበለው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ የሆነው ነገር ተጫዋቾቹን በሚገባ ለማወቅ ዓላማ በተቀረፀለት መልኩ አንድ በአንድ በሆነ ሥልት ተከታታይ ግንኙነት መፍጠርና ተጫዋቹን የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጉ የቻሉትን ነገሮች ወደማጥናት መሸጋገር ሆነ፡፡በግንኙነት ላይ ያደረገው አዲስ አስተሳሰብ ተጫዋቹን ለጨዋታ በሚያነሳሳ መልኩ የግል አፈፃፀሙ ላይ ትኩረት በማድረጉ ከተጫዋቾቹ ምላሾችን ማግኘት ጀመረ፡፡
በሻምፕዮኑ ውድድር የመጨረሻ ወቅት ላይ ተጫዋቾቹ ሃሣብ ለመስጠትና ሃሳብ ለመቀበል ቢሮው በር ላይ ሠልፍ ይዘው መጠባበቅ ጀመሩ፡፡
በሩ ዘወትር ክፍት የሆነ እግዚአብሔር እንዲኖረን መደረጉ ምንኛ ግሩም ነገር ነው?“እናንተም ትጠሩኛለችሁ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ እኔም እሰማችኋለሁ።እናንተ ትሹኛላችሁ በፍጹም ልባችሁም ካሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”(ትንቢተ ኤርምያስ 29፡12-13)
በመሠረቱ እግዚአብሔር “በሬ ክፍት ነው፤ወንበር ሳቡና በአዕምሯችሁ ያለውን ነገር ንገሩኝ”ነው የሚለን፡፡ይሄንን ስናደርግ ምሕረት፤ፀጋና እረፍት ቃል ተገብቶልናል … ሠልፍ መያዝ ደግሞ አይጠበቅብንም፡፡
ተግባራዊ ማድረግ፡-ስፖርትን፤ቡድናችሁን፤ትምህርት ቤትንና የወደፊት ዓላማችሁን በሚመለከት ጥቂት ደቂቃዎችን ወስዳችሁ በሃሣባችሁ ያለውን ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩት፡፡ከዚያ በኋላ እንዴት አድርጎ መልስ እንደሚሰጣችሁ ጊዜ ውሰዱና አዳምጡት፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/