የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

ቀን {{ቀን}} ከ10

የተፈጠርኩት ለእግዚአብሔር ሥራ ነው

“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”ኤፌሶን 2፡10

ስፖርት በሕብረተሰቡ ውስጥ ታዋቂነትን የሚያሰገኘው ከግል ብቃት የተነሳ ነው፡፡ጥሩ ጨዋታ የሚገኘው በመልካም አፈፃፀም ብቻ ነው፡፡አትሌቶች በሜዳም ላይ ሆነ በፍርድ ቤት በተገቢው መንገድ መብታቸው ሊከበር ይገባል፡፡በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ግን ካለን የታዋቂነት ደረጃ አንፃር አይደለም ሥፍራ የሚሰጠን፡፡የሚሰጠን ኢየሱስ ባከናወነው ነገር ላይ በመመስረት ነው፡፡

ታዲያ መልካም ነገርን ለምን እንሰራለን?

እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው የፈጠረው የራሱን ባህርይ በተለየ መንገድ ያንፀባርቅ ዘንድ ነው፡፡ በዘፍጥረት 1፡27 ላይ “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።”ብሎ ይናገራል፡፡

አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ለመለየት ምርጫቸውን ባደረጉበት ወቅት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፡፡ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም የእግዚአብሔር አምሳያነታቸውን አበላሹት፡፡

ወደ ኢየሱስ ቀርበን ንሥሐ በገባንበትና ራሣችንን ባስገዛንበት ቅፅበት ዳግም አዲስ ፍጥረት አደረገን፡፡2ተኛ ቆሮንቶስ 5፡17 ላይ“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፎአል፤እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”በማለት ይናገራል፡፡

በውስጣችን ከሚኖረውና ብርታትን ከሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ የተነሳ  እግዚአብሔር አስቀድሞ ባዘጋጀልን መሠረት መልካምን ሥራን ለመሥራት ነፃ ነን፡፡

እግዚአብሔር መልካምን ሥራ እንድንሰራ ዕቅድ ያዘጋጀልን ድነትን እንድናገኝ ወይም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን እንድናገኝ አይደለም፡፡በኤፌሶን 2፡8-9 ድረስ ባለው ክፍል ውስጥ“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”በማለት ይናገራል፡፡

መልካም ሥራን የምንሰራው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ብለን አይደለም፡፡በደስታ መልካም ሥራን የምንሰራው ነፃነታችንን እናገኝ ዘንድ በደላችንንና ነውራችን ሁሉ ለከፈለልን ክብርን ለመሥጠት ስንል ነው፡፡

መልካም ነገርን እንደገና ወደ እኛ ለማምጣት ሥራውን እየሰራ ነው፡፡ እኛም እግዚአብሔር በዓለም ላይ እየፈፀመ ካለው መልካም ነገር ተካፋይ የመሆን ዕድልን ስላገኘን ደስ ይለናል፡፡መልካም ነገር የምናደርገው ማድረግ ስላለብን ሣይሆን መልካም ነገርን የምናደርገው ለእግዚአብሔር አምልኮና ክብርን ለመስጠት ስንል ነው፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡-በኤፌሶን 2፡10 እንደሚናገረው እግዚአብሔር መልካም ነገርን አዘጋጅቶላችኋል፡፡እነዚያ መልካም ነገሮች ምን እንደሆኑ ለማየት ዙሪያችሁን ትመለከቱ ይሆን?እርሱ  ዘወትር በሥራ ላይ ነው፡፡የት ሥፍራ ላይ ይሆን የምትገናኙት?

ቀን 7ቀን 9

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/