ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና
ከእግዚአብሔር ጋር ሠላም አለኝ
”እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤በእርሱም ደግሞ ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።”ሮሜ 5፡1,2
አሠልጣኛችሁ ትኩረቱን እናንተ ላይ ብቻ እንዲያደርግ ለማድረግ ጥራችሁ ታውቃላቸሁ?
በእነርሱ ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ብቸኛው መንገድ ይሄ ነው ብላችሁ ስለምታስቡና በችሎታችሁ ልክ ለመጫወት ሠላም ሊሰማን ይችላል ብላችሁ ስለምታስቡ የሚያዟችሁን ሁሉ ታደርጉ ነበር፡፡እናንተ ምንም ብታደርጉ፤በርትታቻሁ ብትሰሩም ሆነ ችሎታችሁን እየተሻላላችሁ ብትሄዱም በአሠልጣኙ ፊት በፈለጋችሁት ልክ ተቀባይነት ላታገኙ ትችሉ ይሆናል፡፡
ያ ሲሆን ምን ዓይነት ስሜት ይሰማችኋል? ትረበሻላችሁ ?ተስፋ ያስቆርጣችኋል?እናንተ ሠላም ለማግኘት ስትጥሩ ዘወትር የምትጫወቱትን ስፖርት እንደማይረባ ነገር እንድትቆጥሩት አድርጓችኋል?
በሕይወታችሁ ውስጥ ምንም ዓይነት መልካም ነገር ብትሰሩበእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የማታገኙ የሚመስላችሁ ጊዜ ይኖራል፡፡የሕይወታችሁ ማዕከል መሆን ስለሚፈልግ እግዚአብሔርእንደዚያ ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አሠልጣኝ አይደለም፡፡በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ግን ጣልቃ የገባ ነገር አለ፡፡
ከኃጢአት የተነሣ ከእግዚአብሔር የተለየን ነበርን፡፡
ምንም ያህል መልካም የሆነ ሥራ ብትሰሩም በስፖርቱ ዘርፍ ታላቅ ደረጃ ላይበመሆናችሁ ወይም በጣም ደግ በመሆናችሁም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ልታገኙ አትችሉም፡፡ብታምኑም ባታምኑም የእናንተ እጅግ ምርጥ ሰዎች መሆን ከእግዚአብሔር ጋር ሠላም ለመፍጠር ብቃት እንዲኖራችሁ የማድረግ አቅም የለውም፡፡
ከዚህ ይልቅ አንድ ሰው ይህንን ሠላም ለእናንተ መሥጠት ነበረበት፡፡በሮሜ 15 ፡ 1 በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ሰላምን ያዙ ይላል፡፡ በመስቀል ላይ ስለሞተልን ለኢየሱስ ምስጋና ይድረሰውና አንዴ በእርሱ ካመንን ከእግዚአብሔር ጋር ያንን ሰላም አግኝተናል፡፡
አሁን ግን ስላደረጋችሁት ወይም ስላላደረጋችሁት ሥራ ሣይሆን ኢየሱስ በመሥቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሣ እናንተ በእግዚአብሔር ዘንድ ፀድቃችኋል፤ይቅርታን አግኝታችኋል፡፡
በምናደርጋቸው ነገሮች እንመዘናለን፤ ፍርድ ይሰጠናል፡፡ አፈፃፀማችን በስፖርት ውድድር ወቅት ቢሆን ወይም በሌሎች የሕይወታችን ክፍሎች ውስጥ ለራሣችን ያለን አመለካከት ወይም እግዚአብሔርን ጨምሮ ሌሎች ለእኛ ያላቸው አመለካከት ጭመር የሚለካበት ይሆናል፡፡
ምናልባት በተለያዩ የሕይወታችሁ ዘርፎችውስጥ ውድቀት ስላጋጠማችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ሠላም ያልተስተካከለ ሊመስላችሁ ይችል ይሆናል፡፡በስፖርት ዘርፍ ውስጥ ጥሩ አፈፃፀም ስላላችሁ ወይም ጥሩ ስሜት ስለሚሰማችሁ ብቻ ትክክለኛ ያልሆነ ሠላም ተሰምቷችሁ ሊሆን ይችላል፡፡
ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን ሠላም ውጤታማ ከሆነ አፈፃፀማችሁ ጋር የሚገናኝ ነገር የለውም፡፡መልካም ሰው መሆንም እግዚአብሔርን ለማስደሰትና ከእግዚአብሔር ጋር ፍፁም የሆነ ሠላምን የማስገኛ መንገድ ሊሆንልን አይችልም፡፡
ተግባራዊ እርምጃ ፡-ከአሰልጣኙ/ኟ ወይም በአፈፃፀማቸው ደካማነት ምክንያት ሠላም ስላጡ የቡድን አባላቶቻችሁ እስቲ ለጥቂት ጊዜ አስቡ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/