የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

ቀን {{ቀን}} ከ10

ተስፋ አለኝ

“ነገር ግን ነፍሴ ሆይ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።”መዝሙረ ዳዊት 62፡5

“አንድ አትሌት በኪሱ ውስጥ ገንዘብ አስቀምጦ ሊሮጥ አይችልም፡፡ ተስፋውን በልቡ ውስጥ ሕልሙን በአዕምሮው ሸክፎ ነው መሮጥ የሚኖርበት” ኤሚል ዛቶፔክ

ኤሚል ዛቶፔክ በ1952 እ.ኤ.አ በሄሌሲንኪ ተካሂዶ በነበረው የበጋ የኦሎምፒክ ውድድር ወቅት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘ አትሌት ነበር፡፡በ5000 ሜትር በ10000 ሜትርና በማራቶን ሶስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያገኘ ሰው ነበር፡፡ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ እጅግ የሚያስደንቀው ነገር ውድድሩ ጥቂት ጊዜ ብቻ በቀረበት ወቅት በሕይወቱ የመጀመሪያ የሆነውን የማራቶን ሩጫ ለመወዳደር መወሰኑ ነበር፡፡ያንን ተስፋና የተናገረለትን ሕልሙን ይዞ መሆን አለበት ሩጫውን የሮጠው፡፡

የሚያሳዝነው ነገር አንድ አትሌት ተግባራዊ ሊያደርግ የሚፈልጋቸው ታላላቅ ተስፋዎችና ሕልሞች በአንድ መጥፎ ውድድር ወይም ከባድ የአካል ጉዳት ምክኒያት ፈፅሞ ሊበላሽበት ይችላል፡፡መፅሐፍ ቅዱስ በመፅሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 13 ቁጥር 12 ላይ ፈፅሞ ስለተበላሸና ፍርክስክሱ ስለወጣ ተስፋ ሲናገር “የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፤የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት”በማለት ይናገራል፡፡

አዎ እንደ ክርስቲያኖች ተስፋችን በኢየሱስ ክርስቶሰ ላይ ከመሆኑ የተነሣ ፍርክስክሱ የማይወጣ ተስፋ አለን፡፡ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ሁኔታ ቢከሰት ከእኛ ተስፋችን አይወሰድብንም፡፡በዚች ምድር በምንኖርበት ወቅት ከእርሱ የምንፈልገውን ነገር እንደምናገኝ ማረጋገጫ ይሰጠናል፡፡ከዚች ምድር በምንለይበት ወቅትም ከእርሱ ጋር ሕይወትን ይሰጠናል፡፡እርሱ መንገድ፤እውነትና ሕይወት ነው፡፡በዚህ ዓለምና በሚመጣው ዓለም ተስፋን፤ሠላምንና ፍቅርን ይሰጠናል፡፡

ይህ ተስፋ እግዚአብሔር መሆኑንና የገባቸውን የተስፋ ቃላት ሁሉ እንደሚፈፅመው በተግባር በማሣየት ይሄው ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣዔ ተረጋግጧል፡፡እነዚህ ተስፋዎች የእግዚአብሔር በሆነው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፈው እናገኛቸዋለን፡፡

"በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።”ሮሜ 15፡4

እንደ አትሌቶች ተስፋዎቻችንንና ሕልሞቻችንን ብንፈፅምም ወይም አንዱንም ባንፈፅምም ልንጥለው የማንችለው ተስፋ በዚህ ዓለምና በሚመጣው ሕይወት ውስጥ አለን፡፡

ተግባራዊ እርምጃ ፡-በክርስቶስ ላይ ስላላችሁ ተስፋ ለማሰብና ቀኑን ሁሉ ይህንኑ በተመለከተ ምሥጋናን ለማቅረብ ጥቂት ደቂቃዎችን ውሰዱ፡፡

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/