የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

ቀን {{ቀን}} ከ10

የተመረጥኩና ለእርሱ የተለየሁ ሰው ነኝ

“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ”1ኛ ጴጥሮስ 2፡9

የሚቀጥለውን ጨዋታ መቼ መጫወት እንደምትጀምሩ ጥርጣሬ ውስጥ የገባችሁበትን ጊዜ ታስታውሳላችሁ?

ምናልባትም ችሎታችሁን እያሻሻላችሁ በመምጣታችሁ ገና ጨዋታውን ስትጀምሩአንድ ግብ ማግባት ይገባኛል ብላችሁ አስባችሁ ይሆናል፡፡ምናልባትም ባላችሁ ችሎታ ልክ ካለመጫወታችሁ የተነሣ የመጫወት ዕድላችሁ እየቀነሰ ይሄዳል ብላችሁ አስባችሁም ይሆናል፡፡

ወደዚያ ሁኔታ የሚያመራው ጭንቀት ከባድ ነው….. ከዚያ ስማችሁ ሲጠራ ሰማችሁ፡፡

ከዚህ መልካም ዕድል የተነሣ በጨዋታው ውስጥ የመሣተፍ ብቻ ሣይሆን አሠልጣኙ አንተን ቁልፍ እንደሆነ ሰው ቆጥሮ ሥምህን በመጥራትቡድኑ ስኬታማ ለመሆን ያለኸን ትልቁ ዕድላችን አንተ ብቻ ነህ እያለህ ነው፡፡ተመረጥክ፡፡

የእኛ ሴት ልጆች እያደጉ በነበሩበት ወቅት ከእኛ ሕይወት ጋር የሚስማማ መልዕክት ስለሰማን ምክሩን በልባችን አኖርነው፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ልጆቻችን ከቤት ሲወጡ “ማን እንደሆናችሁና የማን እንደሆናችሁ እንዳትረሱ”እያልን እናሳስባቸው ነበር፡፡

ሴት ልጆቻችንን ማን እንደሆናችሁ አስቡ ስንላቸው አስተዳደጋቸውንና የተማሯቸውን የሕይወት ልምምዶች እንዳይረሱ ነው፡፡ምንጊዜም ቢሆን የተለዩ እንደሆኑ፤ሰዎች በምን ዓይነት መልኩ እነርሱን መቅረብ እንደሚኖርባቸው እንዲያስተውሉና እነርሱም ሌሎች ሰዎችን እንዴት መቅረብ እንዳለባቸው እንነግራቸዋለን፡፡

የማን መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ማሳሰቡ አስፈላጊ ነበር፡፡መጨረሻ ላይ የእኛ መሆናቸው ያበቃል፡፡ልጆቻችን የእኛ የግል ንብረቶቻችን አይደሉም፡፡እንደ ወላጆች የማሣደግ፤የመመገብና የማፍቀር ኃላፊነት ነው የተሰጠን፡፡

በመጨረሻ ተጠሪነታቸው በመጀመሪያ ላይ ለመረጣቸው ይሆናል፡፡የመረጣቸው፤ልዩ የሚያደርጋቸውን ችሎታና ሥጦታ የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ተስፋን ይሰጣቸዋል፤ከጨለማ ይታደጋቸዋል፤እኛም ለዘለዓለም እንወዳቸዋለን፡፡

ከትምህርት ቤት ሜዳ ላይ ብንመረጥ ወይም በዓመቱ ትልቁ ጨዋታ ላይ እንድንሳተፍ በአሠልጣኝ የምንመረጥ ቢሆን መመረጣችን በጨዋታው ውስጥ እንድንሳተፍ ያስችለናል፡፡

በሁሉ ጌታ መመረጥ እና በእርሱ ቡድን ውስጥ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ለማሰላሰል ጥቂት ጊዜ ውሰድ ፡፡ ሐ. ጴጥሮስ ብርሃን ለመሆን እንደተመረጥን እና እግዚአብሔር የጨዋታውን ዕቅድ በእኛ በኩል ‹‹ የእርሱን ድንቅ ስራ እንድንናገር ›› ማድረጉን ይነግረናል ፡፡

ችሎታ የሰጠህን ስትናገር፡-ተስፋን ይሰጥሃል ፣ ከጨለማ ስራ ይጠብቅሃል ለዘለዓለምም ይወድሃል፡፡ እንተም ለእግዚአብሔር ስም ክብርን ታበዛለህ፡፡ ሌሎችንም መመረጣቸውን እንዲመርጡ ትረዳቸዋለህ፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡-ለጥቂት ጊዜ እየሰባችሁ ፀልዩና ይህንን መልዕክት ቢሰሙ ሊበረታቱ ይችላል ብላችሁ ለምታስቧቸው ሰዎ ችበአካል አግኝታችኋቸው ንገሯቸው ወይም ፅሑፉን ስጧቸው፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/