የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል ?ናሙና

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

ቀን {{ቀን}} ከ10

የምኖረው በእምነት ነው

“ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።” ሮሜ 1፡17

እውነተኛ ኑሮን ለመኖር ብቸኛው መንገድ እምነት ነው፡፡የእምነት ትክክለኛ ፍቺ ምንድነው?

እምነት ማለት ነገሩን ከማየታችሁ በፊት በእግዚአብሔር ላይ መታመን ማለት ነው፡፡(ዕብራውያን 11፡1)እምነት ማለት እግዚአብሔር ምን እያደረገ እንዳለ ወይም ለምን ያንን ነገር እንደሚያደርግ ሳንረዳ ዝም ብሎ በእግዚአብሔር ላይ መታመን ማለት ነው፡፡

ልጆች ሁልጊዜም ቢሆን ወላጆቻቸው የሚያደርጉት ነገር እንደማይገባቸው ሁሉ እኛም እግዚአብሔር የሚያከናውነው ነገር ሁልጊዜ ላይገባን ይችላል፡፡ወላጆቻችን ለእኛ የሚያስቡት ነገር እጅግ መልካም ከሆነ ሁሉን ቻይ የሆነው አባታችን ለእኛ እጅግ መልካም ነገር የሚያስብልን መሆኑን ማሰብ አግባብ አይደለም?

እምነት ለእውነት እንድንኖር መንገዱን ይከፍትናል፡፡ምክኒያቱም የምንፈቅደለት ከሆነ እምነት ጭንቀትን፤ጥርጣሬንና ፍርሃትን የማስወገድ ብቃት አለው፡፡ ጭንቀት፤ጥርጣሬና ፍርሃት ከሕይወታቸን ደስታን የሚሰርቁ ነገሮች ናቸው፡፡

ሁለት አማራጮቸ አሉን፡፡1/ዕለት በዕለት የእኛ ሁኔታ ምንም ዓይነት መሻሻል ሊኖረው አይችልም ከሚል ጥርጣሬ የተነሳና የወደፊቱ ኑሯችን ስለሚያስፈራን ነገሮች እንዴት ወደ መልካምነት ሊለወጡ ይችሉ ይሆን?እያልን ሰንጨነቅ መዋል2/በእምነት መኖር፤በሕይወታችን ጉዞ እየተጓዝን እያለን እግዚአብሔር ሁኔታችንን ሊለውጠው እንደሚችልና የምንሻቸውን ነገሮች ሁሉ ሊያሟላልን እንደሚችል በመተማመን በእምነት መኖርና (ፊሊጵስዩስ 4፡19)ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሆነ(ሮሜ 8፡28) በማወቅ በእምነት መኖር ነው፡፡

ስለዚህ እምነት በስፖርት ላይ ተግባራዊ የሚሆነው እንዴት ነው?ለምሣሌ ከጉዳት የተነሣ የጨዋታ መርሐ ግብሩ ስለተበላሸበት አንድ አትሌት ወይም ደግሞ ባልጠበቀው ሁኔታ በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ ስለተባረረ አንድ አሠልጣኝ እንውሰድ፡፡በመሠረቱ እነዚህ ሰዎች ለምን ይሄ ሆነ? ብለው ቢያጉረመርሙ አይፈረድባቸውም፡፡

እምነት ማለት የተወሰኑ ነገሮች በሕይወታችሁ ወስጥ ለምን እንደተፈጠሩ ልታውቁ እንደማትችሉ በሞኝነት መቀበልን ያካትታል፡፡እምነት ማለት በእግዚአብሔር ማንነት ላይ፤በተስፋ ቃሎቹ ላይ ማተኮርን መምረጥና እርሱን የሕይወታችሁ ማዕከል እንዲሆን በማድረግ በእርሱ ላይ መታመንን ያካትታል፡፡

ተግባራዊ ማድረግ፡-2ተኛ ቆሮንቶስ 2፡7ን በቃላችሁ ያዙት፡፡“እንግዲህ ሁልጊዜ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና” ሌላ ጊዜ ስለ አንድ ነገር መጨነቅ ስትጀምሩ ጭንቀታችሁ ከላያችሁ ላይ እስኪወገድ ድረስ ይሄንን ጥቅስ ደጋግማችሁ ተናገሩት፡፡

ጭንቀታችሁን በእግዚአብሔር ህልውና እንዲተካ ማድረግ በእምነት መኖር ለመጀመር ብቸኛው መንገድ ነው፡፡

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

ትግል እና ድል ፡- እግዚአብሔር ስላለኝ ነገር ምን ይላል  ?

እንደ አንድ አትሌት ሌሎች ሰዎች ሕይወታችሁንና አፈፃፀማችሁን በሚመለከት በሚያወሩበት ዓለም ውስጥ ነው የምትኖሩት፡፡ይህ የ11 ቀናት ዕቅድ እግዚአብሔር እናንተን እንደ ልጅ በመቁጠር ለእናንተ የሰጠውን ነገር እንድትረዱ ያግዛችኋል፡፡የሚሰጠው ተስፋ ያለው ሕይወትን፤ደህነትን፤ሠላምንና እገዛን ነው፡፡በእነዚህ ብርቱና ሕይወት ለዋጭ የሆኑ አስተሳሰቦችን የታጠቁ አትሌቶች ልዩ ይሆናሉ፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረብን "Athletes In Action" ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ይህንን ይጎብኙ: https://athletesinaction.org/struggle-and-triumph/