የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የፋሲካ ታሪክናሙና

The Story of Easter

ቀን {{ቀን}} ከ7

እሁድ

በዚህ አስገራሚ ቀን ስለ መስቀሉ ፣ ባዶ መቃብሩ እና ስለሰጠን ነገር ሁሉ በማሰላሰል እሳልፋለን ፡፡ እንዲሁም በተጨማሪ ዛሬ “ሂዱና ደቀ መዛሙርትን አፍሩ . . .” ተብለን በተጠራነው ሥራ ላይም እናሰላስል። ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ንፁህ ወንጌልን ያስተላለፈው እንድንቀበለው ብቻ ሳይሆን ፣ ለሌሎችም የሚተላለፍ መልካም የምሥራች ዜና ስለነበረ ነው ፡፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ሌሎች ደቀመዛምርቶች ብቁ እንዲያረጉና ፍሬ እንዲያፈሩ አዘጋጅቷቸዋል ፡፡ ደቀመዝሙር የሆኑት ሰዎች እራሳቸው ሌላ ደቀመዛሙርቶችን ሲያፈሩ ስለነበረ ይህ ተግባር በትክክል እንደሰራ ማወቅ እንችላለል። እናም ይህ ተግባር ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ሲተላለፍ ቆይቷል። ግን ምናልባት በሁሉም ትውልዶች ( በእርግጠኝነት ግን በእኛ ትውልድ ውስጥ) የምናሰራጨው ወንጌል አንዳንዴ ወደ ደካማ ነገር ይለወጣል ፡፡ እውነተኛ ፍሬን ከማፍራት ይልቅ ዘር የሌላቸውን ፍሬዎች እናመርታለን። ዛሬ ለተቀበልነው ጸጋ እግዚአብሔርን በምናመሰግንበት እና በምናመልክበት ጊዜ ያን የተሰጠንን ጸጋ ለሌሎች አስተላልፈን ፈተናውን እንድናልፍና ታላቁን ተልእኮ እንድንወጣ እንጸልይ፡፡
ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

The Story of Easter

የሕይወትዎ የመጨረሻ ሳምንት መሆኑን ቢያውቁ ሳምንቱን እንዴት ያሳልፋሉ? ኢየሱስ በሰው አምሳል በምድር ላይ በነበረው የመጨረሻ ሳምንት በማይረሱ አፍታዎች ፣ በተፈፀሙ ትንቢቶች ፣ በጥልቅ ጸሎት ፣ በጥልቅ ውይይት ፣ በምሳሌያዊ ድርጊቶች እና ዓለምን በሚለውጡ ክስተቶች የተሞሉ ነበሩ፡፡ ከፋሲካ በፊት ባለው ሰኞ እንዲጀምር ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ የላይፍ.ቸርች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕቅድ የቅዱሱ ሳምንትን ታሪክ እንዲያውቁ ይመራዎታል።

More

ይህንን ዕቅድ ላቀረበልን ላይፍ.ቸርችን ማመስገን እንወዳለን፡፡ ስለ ላይፍ.ቸርችን የበለጠ ለመማር ከፈለጉ እባክዎን ይህን ድህረገጽ ይጎብኙ፡www.Life.Church