የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የፋሲካ ታሪክናሙና

The Story of Easter

ቀን {{ቀን}} ከ7

አርብ

ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 3 ላይ “ክርስቶስንና የትንሳኤውን ኃይል እንዲሁም መከራውን በህብረት መካፈልን ፣ በሞቱም እንደ እርሱ መሆንን” ብሎ የሚፈልገውን ፅፉል፡፡ ምንም እንኳን ይህንን አሰቃቂ ትዕይንት ለመካፈል ፍቃደኛ መሆንን ለማመን ቢያዳግትም ፣ የዚህ ታሪክ ተዓምር ግን ክርስቶስን በእውነት ማወቅ እንድንችል ይረዳናል። ሰላም ፣ ደስታ ፣ ፀጥታና ፀጋ በዓመፃ ላይ ሁሉ ሲያበራ ስንመለከት ፣ በእርሱ ሞት ውስጥ እንደ እርሱ የመሆንን ውበት እናያለን። በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ በመታመኑ ህይወቱ እንዴት እንደቀለለት። ለውድ ጓደኛው አደራ ከሰጠው ከእናቱ በቀር ምንም ምድራዊ ነገር አልነበረውም ፡፡ የእርሱ ብቸኛ ንብረት በቁማርተኛው ጠባቂ ላይ የወደቀው ልብሱ ነበር። ያ ቀላልነት። ያ ግልጽ የሆነ ትኩረት። ያ ለእግዚአብሔር ዓላማ የነበረው ታማኝነት። ያ በአባቱ ላይ ያለው ሙሉ እምነት፡፡ ያንን ነው በጉጉት መጠበቅ።
ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

The Story of Easter

የሕይወትዎ የመጨረሻ ሳምንት መሆኑን ቢያውቁ ሳምንቱን እንዴት ያሳልፋሉ? ኢየሱስ በሰው አምሳል በምድር ላይ በነበረው የመጨረሻ ሳምንት በማይረሱ አፍታዎች ፣ በተፈፀሙ ትንቢቶች ፣ በጥልቅ ጸሎት ፣ በጥልቅ ውይይት ፣ በምሳሌያዊ ድርጊቶች እና ዓለምን በሚለውጡ ክስተቶች የተሞሉ ነበሩ፡፡ ከፋሲካ በፊት ባለው ሰኞ እንዲጀምር ተደርጎ የተዘጋጀው ይህ የላይፍ.ቸርች የመጽሐፍ ቅዱስ ዕቅድ የቅዱሱ ሳምንትን ታሪክ እንዲያውቁ ይመራዎታል።

More

ይህንን ዕቅድ ላቀረበልን ላይፍ.ቸርችን ማመስገን እንወዳለን፡፡ ስለ ላይፍ.ቸርችን የበለጠ ለመማር ከፈለጉ እባክዎን ይህን ድህረገጽ ይጎብኙ፡www.Life.Church