አሰማምን መማርናሙና

አሰማምን መማር

ቀን {{ቀን}} ከ6

በሚሰማ ነገር ልብህ አይውደቅ

ዮሴፍ ያዕቆብ አስራ አራት ዓመት ሙሉ ዋጋ በመክፈል ከሚወዳት ሚስቱ የወለደው ብርቅ ልጁ ነው። ከሌሎቹ ልጆቹ የበለጠ  ይወደውና ይንከባከበው ነበር፤ ጌጠኛ ልብስ ይገዛለት ነበር፤ ከእርሱ ፊት እንዲርቅ አይፈለግም፤ እንዲሁም ከብት ጠብቅ ተብሎ አይላክም። የዮሴፍ ወንድሞች ከወጡ ሰንበትበት ብለዋል። ያሉበት አድራሻ በትክክል አይታወቅሞ። ከዮሴፍ ሌላ ልጅ ቤት ውስጥ የለም። ያዕቆብ የሚፈተንበት ጊዜ መጣ። ዮሴፍ ወንድሞቹን ጠይቆ እንዲመጣ ተላከ። 

ነገር ግን የያዕቆብ ልጆች በብዙ ሕብር ያጌጠች ቀሚሱን በደም አጨማልቀው አመጡለት። ያዕቆብ ብዙ ማስረጃ አልፈለገም። አንድ ፍሬ ልጁ በአውሬ እንደተበላ አረጋገጠ። እርግጥ ነው የጠበቁት ቀርቶ ያልጠበቁት ነገር ሲከሰት ማዘን የማይቀር ጉዳይ ነው። ያዕቆብ በሀዘን ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለበሰ፤ ለብዙ ቀን አለቀሰ፤ እያዘነም ወደ ቀብር ለመሄድ ወሰነ። ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ሰዎች ያመጡለትን መረጃ አመነ። 

ዮሴፍ  በልጅነቱ የተቀበለውን ራዕይ ለአባቱ ሲያጫውተው ትርጉም ከመስጠት ባለፈ ፍፃሜውን በብሩህ ተስፋ ይጠባበቅ ነበር። በዮሴፍ ላይ የተከሰተ ፈተና ራዕይ ማስፈፀሚያ ነበር። ዮሴፍ ለሹመት ወደ ንግሥና ዙፋን እየገሰገሰ ነው። ትላንት መርዶ ያመጡለት  ሰዎች ዮሴፍ በግብፅ ምድር  ላይ  ገዢ  ሆኖዋል አሉት። ያዕቆብ ደነገጠና አላመናቸውም። ነገር ግን ልጁ የሰደዳቸውን ሰረገሎች ሲመለከት ነፍሱ በሕይወት ተሃድሶን አገኘች። 

ያዕቆብ ትናንት የመጣለት ዜና በዮሴፍ ሕልም እግዚአብሔር ያሳየውን ረስቶ በሰማው ተደናግጦ እንደነበረና ከዛም በዮሴፍ ገዢነት ሕይወቱ እንደታደሰች፤ እኛም እንደ አማኝ በምንሰማው ነገር ልባችን ሊወድቅ አይገባም፡፡ ነገር ግን በአማኝ ሕይወት  ላይ  የሚመጣ ፈተና የእግዚአብሔር ዓላማ ማስፈፀሚያ  እንጂ ለሞትና ለውድቀት እንዳይደለ ተረድተን በእምነት እንቁም፡፡

የሕይወት ተዛምዶ

ፈተናዎች ወደ ሕይወታችን ሲመጡ በመጀመሪያ የሚሰማን ምንድነው? ቆም ብለን እግዚአብሔር የተናገረንን እናስታውስ፡፡

ፀሎት

እግዚአብሔር ሆይ፣ በሚያልፍ ጊዜያዊ  ፈተና ልባችን ተይዞ ከአንተ ሀሳብ እንዳንወጣ ጠብቀን!


ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

አሰማምን መማር

አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org