አሰማምን መማርናሙና

አሰማምን መማር

ቀን {{ቀን}} ከ6

ምላሽ እንስጥ 

ሳይንስ በበረሃ ሙቀት፣ ድምጽ የበለጠ ጎልቶ እንደሚሰማና በበለጠ ፍጥነት እንደሚሄድ ይነግረናል። ከሙቀቱ የተነሳ ሞሎኪውሎች በፍጥነት ስለሚንቀሳቀሱ ድምጽንም እንዲሁ በፍጥነት ያጓጉዛሉ። እንግዲህ ሙቀቱና ዝምታው አንድ ላይ በመሆን ጭር ያለውን ምድረበዳ ድምጽን ለመስማት ምቹ ቦታ ያደርጉታል። ሳይንስ ወደ እግዚአብሔር መንገዶች ቀስ በቀስ እየደረሰ ነው! 

እግዚአብሔር አንዳንዴ ድንገት በምድረበዳ እንዳለን እስኪሰማን ድረስ የተለያዩ ነገሮችን ከሕይወታችን የሚያስወግድባቸው ወቅቶች አሉ። የሚደግፉንን እንዲሁም ምቾት የሚሰጡንን ነገሮች ከሕይወታችን መውሰድ ይጀምራል። በዚህ ንባብ ክፍል ውስጥ የሰንበት በዓላትን ጭምር እንዲህ ሲያደርግ እናያለን። አስተዋላችሁት? እነዚህን ነገሮች የሚወስዳቸው ለእኛ መጥፎ ስለሆኑ ሳይሆን ሌሎች የተሻሉ ነገሮች ለእኛ ስላለው ነው። ነገር ግን አዲሶቹን ነገሮች ለእኛ ከማሳወቁ በፊት በምድረበዳ - “በአኮር ሸለቆ” - እኛን ሊናገረን ይፈልጋል። በዛም በደንብ እንደምንሰማው ስለሚያውቅ እግዚአብሔር ብዙ ነገሮችን በምድረበዳ የነግረናል። 

እግዚአብሔር ህዝቡን ከግብጽ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸው በምድረበዳ ነበር፣ ምክንያቱም በዛ እነርሱን ለመናገር ነው። እንዴት መኖር እንደሚገባቸውና በተስፋይቱ ምድር እንዲበለጽጉ ስለ ትዕዛዛቱና የሰንበት ስርዓቶቹን ነገራቸው። (ሕዝቅኤል 20:10-12)

እግዚአብሔር ሊናገረንና ሊያድሰን አሁን ሁላችንም እያለፍንበት ባለው ምድረበዳ እየመራን ይሆን? ለድምጹ ምላሽ እንሰጥ ይሆን? 

የሕይወት ተዛምዶ

እግዚአብሔር እየተናገረ ነው። ምድረበዳችንን እንቀድሰው እናም ጊዜያችንንና አትኩሮታችንን ለድምጹ ምላሽ ለመስጠት እናውለው። 

ፀሎት 

ጌታ ሆይ ስትናገር ምላሽ እንድሰጥ እርዳኝ። አሜን!


ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

አሰማምን መማር

አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org