አሰማምን መማርናሙና
የመስሚያ መሳሪያ
በአሁኑ ጊዜ የችግር ወሬና ዜና አጥለቅልቆናል፡፡ ከዚህ አንፃር ዛሬ ሌላ ነገር መስማት ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰናል፡፡ ሆኖም የምንሰማው ነገር ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ባንችልም የመስሚያ መሳሪያን በመጠቀም እንዴት እንደምንሰማ መምረጥ የሚያስችለንን መንገድ ላቀርብላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ የመስሚያ መሳሪያ በደንብ መስማት ለማይችሉ ሰዎች ድምፅን ከፍ በማድረግ እንዲሰማቸው ይረዳል፡፡ የሚሰሙትን ነገር አይለውጥም፤ ነገር ግን የሚሰሙትን የድምፅ መጠን በማሻሻል በደንብ እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ተግባሩ በሚሰሙት ነገር ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ሳይሆን እንዴት እንደሚሰሙ ተፅዕኖ ማድረግ ነው፡፡
በተመሳሳይ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ ወንጌል 8፡18 ላይ ‹‹እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ›› ይላል፡፡ የምትሰሙትን ነገር ተጠንቀቁ ሳይሆን የምትሰሙትን ነገር እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ ነው ያለው፡፡ የምንሰማበት መንገድ ለሰማነው ነገር የምንሰጠውን ምላሽ ይወስናል፡፡ ስለዚህ አሁን እንዴት ነው መስማት ያለብን? የመስሚያ መሳሪያችን ምንድነው?
መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር ‹‹እንግዲህ እምነት የሚገኘው መልዕክቱን ከመስማት ነው፤ መልዕክቱም ከእግዚአብሔር ቃል ነው›› ይላል፡፡ (ሮሜ 10፡17) በዚህ ትርጉም መሰረት የእምነት ምላሽ የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል በመስማት ወይም እንደ እግዚአብሔር ቃል በመስማት እንጂ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ብቻ አይደለም፡፡ ቃሉ የምንሰማውን ነገር ትርጉም ይሰጥልናል፡፡ ሌሎች ችግር ሲሰሙ እናንተ ግን መልካም ዕድልን ትሰማላችሁ ( ኤፌ. 5፡16) እነርሱ ግራ መጋባት ሲሰማቸው እናንተ ግን ተስፋ ይሰማችኋል፤ እነርሱ ነገራቸው እንዳበቃ ሲሰማቸው እናንተ ግን አዲስ ጅማሬ ይሰማችኋል ምክንያቱም እናንተ ስትሰሙ በቃሉ ትሰማላችሁ፡፡ እናንተ የመስሚያ መሳሪያው አላችሁ!!! ስለዚህ አሁን የመስሚያ መሳሪያችሁን፤ ማለትም የእግዚአብሔርን ቃል ተጠቅማችሁ ዜናዎችን መስማት፣ ሁኔታዎችን ማገናዘብ፣ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ውይይት ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
የሕይወት ተዛምዶ
በየዕለቱ የዓለምን ነገር ከመስማታችን በፊት ከእግዚአብሔር ቃል መስማትን እንለማመድ፡፡ የመስሚያ መሳሪያችሁን በመጀመሪያ ያዙ፡፡
ፀሎት
ጌታ ሆይ፣ የዓለምን ጩኸት ዝም አሰኝቼ በሕይወቴ ላይ በሰጠኸኝ ውድ በሆነው ቃል ኪዳንና ምስክርነት እንድኖር እርዳኝ፡፡ አሜን!
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org