አሰማምን መማርናሙና

አሰማምን መማር

ቀን {{ቀን}} ከ6

ይሰማችኋል?

ደስታን እንኳን ቸል ልንለው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ስቃይ ትኩረታችንን አጥብቆ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር በደስታችን ጊዜ ቀስ ብሎ ለህሊናችን ይናገራል፣ በስቃያችን ግን ጮክ ብሎ ይናገራል፡- ይህ መስማት የተሳነውን ዓለም መቀስቀሻ ትልቅ ድምፅ ማጉያው ነው፡፡ ሲ.ኤስ ልዊስ፣ ዘ ፕሮብሌም ኦፍ ፔይን

አንዳንድ የቤተክርስቲያን ታሪኮች ሐዋሪያው ዮሐንስ ሁለት ጊዜ በፈላ ዘይት ውስጥ እንደተቀቀለ እና በህይወት እንደተረፈ ይጠቁማሉ፡፡ በህይወት ከተረፈ በኋላ ፍጥሞ ወደምትባል ደሴት ተሰዶ ነበር፡፡ በፍጥሞ ደሴት ላይ ሆኖ ነው ዮሐንስ የራዕይን መፅሀፍ የተቀበለው እና የፃፈው፡፡ “…ቀደም ሲል እንደ መለከት ሲናገረኝ የሰማሁት ድምፅ፣ ወደዚህ ና….” (ራዕይ 4፡1)

ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ድምፅ የተለማመደ እና የሚያውቅ ነበር፡፡ ይህ ልምምዱ ነበር ዮሐንስን በህመሙ እና በጭንቀቱ ላይ ኢየሱስ ሲናገር ድምፁን እንዲለየው እና እንዲሰማው ያደረገው፡፡ ብዙዎቻችን በችግር ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት እንጓጓለን፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ድምፅ ድምፁን መለማመድን ይጠይቃል፡፡

እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬ በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል፡፡ (ሶፎኒያስ 3፡17)

የእግዚአብሔር ድምፅ ለእኛ አስቀድሞ ዘመረ፡፡ የፍቅሩ ዜማ ጮክ ያለ ነው! ለፍቅሩ ምላሽ እግዚአብሔር ለእርሱ ድምፅ ጆሮዎቻችንን ያሰለጥንልናል፡፡ የልብ ምታችሁ የእርሱን አስቸኳይ ነገር፣ የአካል እንቅስቃሴውን እና የንግግሮቹን ድግግሞሽ ያውቃቸዋል፡፡ በየጠዋቱ የእርሱን ድምፅ ለመስማት ጆሮዋችሁን ዘንበል ማድረግን ልምዳችሁ ስታደርጉ በሌሊት ጨለማ ድምፁን ለመለየት አትቸገሩም፡፡ እርሱ ሲዘምር መደነስን ከተማራችሁ እና ህይወታችሁን እርሱ በሚመክራችሁ ከመራችሁ፤ በህመማችሁ ሲጠራችሁ ምላሽ ለመስጠት አተቸገሩም፡፡ 

በየእለቱ እግዚአብሔር ቀላል የሹክሹክታ ድምፁን ሲያሰማ መከተል፣ መስማት እና ማክበር ተማሩ፤ ይህንን ስታደርጉ በችግራችሁ ጊዜ የእርሱ ድምፅ እንደመለከት ወደ እናንተ ይመጣል፡፡

የሕይወት ተዛምዶ

በዚህ ሳምንትት በትንንሽ ነገሮች መንፈስ ቅዱስን ለመስማት ይሞክሩ፡፡ ስለእናንተ ሲዘምር መስማት ተለማመዱ፡፡

ፀሎት

መንፈስ ቅዱስ ስለትንንሽ ነገሮች አንተን ችላ ስላልኩህ ይቅር በለኝ፡፡ ለአንተ ሹክሹክታ መንፈሴን አንቃው፡፡


ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

አሰማምን መማር

አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org