አሰማምን መማርናሙና
የመረጃ ጦርነት
በአሁኑ ዘመን የሚቀርቡልንን መረጃዎችን መመርመርና መለየት ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ቪዲዮዎች በሃሰተኛ መልኩ በቀላሉ በሚቀነባበሩበት፣ እውነታዎች ተቆራርጠውና ኤዲት ተደርገው በሚቀርቡበት ዘመን ምን ያህል የምንሰማውን ነገር ማመን እንችላለን? ብዙ አካላት አንድን ክስተት በፈለጉት መልክ እኛን ለመመገብ ዕድል ያላቸው ይመስላል። እንደ መረጃ ወይም ዜና ሆኖ የሚቀርቡት አብዛኞቹ ነገሮች አጀንዳ አዘል አስተያየቶች ናቸው፡፡ እንደ ፈረስ ልጓም በፈለጉት አቅጣጫ ስሜታችንን ለማዘንበል ይሞክራሉ፡፡
በዘፍጥረት 37 እንደምንመለከተው የሳለ የመለየት አቅም ሳይኖረን፣ የቀረቡልን መረጃዎች ምን ያህል ከእግዚአብሔር እውነት ወደ ራቀ ድምዳሜዎችና ውሳኔዎች ሊወስዱን እንደሚችሉ እናያለን። የምናምነው “እውነት” ነባራዊ ሕይወታችንን ይወስናል። ስለዚህ “የእውነት” መጋቢያችን እንዲሆን የፈቀድንለት ነገር የምላሻችንም አቀነባባሪ ይሆናል።
“የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ የሚሰማውን ብቻ ይናገራል፤ እንዲሁም ወደ ፊት ስለሚሆነው ይነግራችኋል” ዮሐንስ 16:13
ኢየሱስ በራሳችን “እውነትን” ማግኘት እንደማንችል ያስረዳል። እንዲሁም የዜና ማሰራጫዎችን በመመልከት ወይም ፌስቡክና ዩቱብን በመጎርጎር “እውነትን” ማግኘት አንችልም። ወደ “እውነት” በመንፈስ ቅዱስ መመራት አለብን።
“ከሰማይ የተገናኘ እውነት” አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ቢኖር - አሁን ነው! “ከሰማይ የተገናኘ እውነት” አሁን እየተከናወነ ያለውን ነገር የማሳለፍ አቅም ብቻ ሳይሆን፣ ለሚመጣውም “ነገር” የመሻገር ኃይል ይሰጠናል። መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠን ይህ “ከሰማይ የተገናኘ እውነት” ነው። ነፃ የሚያወጣው እውነት ነው (ዮሐንስ 8፡32)።
ያለ መንፈስ ቅዱስ በሀሳቦችና በመረጃ ጭጋጎች ውስጥ ዓላማ ቢስ የሆነ አዙሪት ውስጥ እናልፋለን እንጂ የእውነትን ሽልማት በጭራሽ አንይዛትም። የሰፊውን ሕዝብ አመለካከት ከመከተል ሻገር ማለት ከፈለግን የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ለመስማት፣ ለማመንና ለመከተል የልባችንን ጆሮዎች ማስለመድ አለብን። መንፈስ ቅዱስ ለእውነት ታማኝና አስተማማኝ መሪ ነው።
የሕይወት ተዛምዶ
በዙሪያችሁ ላሉት አስተያየቶች በራችሁን ዝጉ። ከዚያ በኋላ? ፀልዩ፣ አዳምጡ፣ ታመኑና ተከተሉ!
ፀሎት
መንፈስ ቅዱስ፣ አሁን ወደ አንተ ምሪት ልቤን እከፍታለሁ። እና ሁሉም አስተያየቶች ወደ ደቡብ የሚጓዙ ቢሆንም፣ አንተን ወደ ሰሜን ለመከተል እታመናለሁ!
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org