የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አሰማምን መማርናሙና

አሰማምን መማር

ቀን {{ቀን}} ከ6

የውሃ ጋኖቻቸሁን ሙሉ!

ሃቀኞች ከሆንን፣ እኛ ቁጭ ብለን ችግራችንን ሁሉ እግዚአብሔር መጥቶ እንደሚፈታልን የምናስባቸው ፀሎቶቻችን ምን ያህሎቹ  ናቸው? አህ… አዎ፣ በጉልበታችን  ሆነን “የሰነፍ ሰው” ፀሎቶች ስንፀልይ  እንዳንገኝ መጠንቀቅ አለብን። ኢየሱስ በሂደቱ ውስጥ እኛን በማካተት  ይደሰታል። በታዛዥነት በመራመድና በእምነታችን ውስጥ ሲሠራ በመመልከት የራሳችን ተዓምር አካል እንድንሆን ይፈልጋል።

በዮሐንስ 2 ውስጥ ያሉብንን ችግሮችና ፍላጎቶች እንዴት እንደምንፈታ በተመለከተ ማርያም ታላቅ መመሪያ ትሰጠናለች፣ “[ኢየሱስ] የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ”፡፡

ውሃው ወደ ወይን የተቀየረበት ታሪክ ውስጥ የሚያስገርመው ነገር ኢየሱስ የሰዎችን ተሳትፎ መጠየቁ ነው። የምናየው ነገር ኢየሱስ መመሪያዎችን ሲሰጥ ሰዎች ደግሞ በፍጥነት ሲታዘዙ ነው። እርሱ “ጋኖቹን ውሃ ሙሏቸው” ይላል እነርሱም ጉዟቸውን ወደ ውሃው ምንጭ አደረጉ፣ ውሃውን መልሰው አጓጉዘው “ጋኖቹንም እስከ አፋቸውም ሞሏቸው”። መፍትሄው ምንም ያህል አስቂኝ እንደሆነ ቢያስቡም ...ዝምብለው አደረጉት።

ኢየሱስም እንዲህ አለ “ከላዩ ቀድታችሁ ለድግሱ ኀላፊ ስጡት”፣ ቃሉ ላይ በመጀመሪያ ተዓምሩን ለማረጋገጥ ወይኑን እንደ ቀመሱ አይናገርም። በአገልጋዮቹ መታዘዝና እምነት ውስጥ ኢየሱስ ሠራ። ለድግሱ ኀላፊም በቀረበለት ጊዜ በወይን ጠጁ ተገረመ፣ የሙሽራው መልካም ስም ተጠብቆ መቆየት ብቻ ሳይሆን ክብርም አገኘ።

ኢየሱስ ለችግሮቻችንና ለፍላጎታችን መፍትሄዎች አሉት፣ እርሱ መልስ ነው፣ ግን እርሱ እኛን ሲመራን እያዳመጥን ነው? ብዙ ሰዎች ከባድ ችግሮችና እጦት ውስጥ ባሉበት ወቅት የእግዚአብሔር ህዝብ መፍትሄ አምጪ ሆነው ይገኛሉ? እኛስ ድምፁን በጠበቀ መልኩና እምነተ-ሙሉ ሆነን ኢየሱስ ሲመራን ያለ ማንገራገር እርምጃ እንወስድ ይሆን?

የሕይወት ተዛምዶ

በሚያጋጥሟችሁ ችግሮች መካከል ምን ማድረግ እንደምትችሉ ራሳችሁን ጠይቁ። ምን የመታዘዝ እርምጃ መውሰድ ትችላላችሁ?

ፀሎት

ኢየሱስ ሆይ፣ ተአምራትን ታደርግ ዘንድ ለድምፅህ ታዛዥ እንድሆንና በእምነት በመራመድ የውሃ ጋኖቼን እስከ አፋቸው ለመሙላት ፈቃደኛ እንድሆን እርዳኝ።



ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

አሰማምን መማር

አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ “ድምፆች” ወደ እኛ የሚመጡበት ጊዜ ነው። ድምፁንና ምሪቱን ከእግዚአብሔር መስማት ላይ በማተኮር የሚቀጥሉትን 6 ቀናት ያሳልፉ። የእርሱን የእውነት ቃል ጆሮዎቻችሁንና ነፍሳችሁን በሚያድስ አዲስ መንገድ ይገናኙ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org