2 ዜና መዋዕል 35:1-15

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፋሲካን አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካው በግ ታረደ። ካህናቱን በየአገልግሎታቸው መደበ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎትም እንዲተጉ አበረታታቸው። እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። በእስራኤል ንጉሥ በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን በተጻፈው መመሪያ መሠረት፣ እንደየቤተ ሰባችሁ በክፍል በክፍላችሁ ራሳችሁን አዘጋጁ። “ሌዋውያን ባልሆኑ ወንድሞቻችሁ አንጻር እንደየቤተ ሰቡ ምድብ በተቀደሰው ስፍራ ቁሙ፤ ለእያንዳንዱም የቤተ ሰብ ምድብ ሌዋውያን ይኑሩት። ከዚያም የፋሲካውን በጎች ዕረዱ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘውም መሠረት ዕርዶቹን ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።” ኢዮስያስም እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆኑ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ በግና ፍየል እንዲሁም ሦስት ሺሕ ወይፈን ከንጉሡ ሀብት ሰጠ። ሹማምቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በገዛ ፈቃዳቸው አዋጥተው ሰጡ። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቆች የሆኑት ኬልቅያስ፣ ዘካርያስና ይሒኤልም ለፋሲካ መሥዋዕት የሚቀርቡ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ በግ እንዲሁም ሦስት መቶ ወይፈን ሰጡ። ደግሞም ኮናንያ፣ ወንድሞቹ ሸማያና ናትናኤል እንደዚሁም የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸቢያ፣ ይዔኤልና ዮዛባት ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆኑ ዐምስት ሺሕ በግና ፍየል ዐምስት መቶም በሬ ለሌዋውያኑ ሰጧቸው። የአገልግሎቱ ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ፣ ንጉሡ ባዘዘው መሠረት ካህናቱ በየክፍላቸው ከተመደቡት ሌዋውያን ጋራ ቦታ ቦታቸውን ይዘው ቆሙ። የፋሲካው በጎች ታረዱ፤ ካህናቱ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የበጎቹን ቈዳ ገፈፉ። በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ እንደየቤተ ሰቡና እንደየምድቡ ለሕዝቡ ለመስጠት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ፤ ወይፈኖቹንም እንደዚሁ አደረጉ። እነርሱም የፋሲካውን መሥዋዕት በሥርዐቱ መሠረት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸት፣ በሰታቴና በድስት ቀቀሉ፤ ወዲያውኑም ለሕዝቡ አደሉ። ከዚህ በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ ዝግጅት አደረጉ፤ ምክንያቱም ካህናቱ የአሮን ልጆች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሥቡን እስከ ሌሊት ድረስ ያቀርቡ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ዝግጅት አደረጉ። መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር።

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢዮስያስም ለእግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ፋሲካ አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ። ካህናቱንም በየሥርዓታቸው አቆመ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ አጸናቸው። እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ተዘጋጁ፤ እንደ ሕዝቡም ልጆች እንደ ወንድሞቻችሁ በየአባቶቻችሁ ቤቶች ሆናችሁ በመቅደሱ ቁሙ፤ የሌዋውያንም ነገድ በየወገናቸው እንደ ተከፈሉ እናንተም ተከፈሉ፤ ፋሲካውንም እረዱ፤ እናንተም ተቀደሱ፤ እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ የተናገረውን ቃል ያደርጉ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።” ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም ወይፈኖች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ። መሳፍንቱም ለሕዝቡና ለካህናቱ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቆች፥ ኬልቂያስ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ። አገልግሎቱም ተዘጋጀ፤ ካህናቱም በስፍራቸው፥ ሌዋውያኑም በየክፍላቸው እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ቆሙ። ፋሲካውንም አረዱ፤ ሌዋውያኑም ቁርበቱን ገፈፉ፤ ካህናቱም ከእጃቸው የተቀበሉትን ደም ረጩ። በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ። ፋሲካውንም እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸትና በሰታቴ፥ በድስትም ቀቀሉ፤ ለሕዝቡም ልጆች ሁሉ በፍጥነት አደረሱ። ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ። የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍ፥ እንደ ኤማን፥ የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢዮ​ስ​ያ​ስም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፋሲካ አደ​ረገ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ አረዱ። ካህ​ና​ቱ​ንም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው አቆመ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አጸ​ና​ቸው። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መሥ​ራት የሚ​ች​ሉ​ትን ሌዋ​ው​ያን ራሳ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ያ​ነ​ጹና ቅድ​ስ​ቲ​ቱ​ንም ታቦት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞን በሠ​ራው ቤት ውስጥ እን​ዲ​ያ​ኖሩ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ኢዮ​ስ​ያስ አለ፥ “በት​ከ​ሻ​ችሁ የም​ት​ሸ​ከ​ሙት አን​ዳች ነገር አይ​ኑር፤ አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሕዝ​ቡን እስ​ራ​ኤ​ልን አገ​ል​ግሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዳዊት እንደ አዘዘ፥ ልጁም ሰሎ​ሞን እንደ አዘዘ በየ​ሰ​ሞ​ና​ች​ሁና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ቤቶች ተዘ​ጋጁ፤ እንደ ሕዝ​ቡም ልጆች እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በየ​አ​ባ​ቶች ቤቶች አከ​ፋ​ፈል በመ​ቅ​ደሱ ቁሙ፤ እን​ዲ​ሁም ለሌ​ዋ​ው​ያን በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት አከ​ፋ​ፈል ይሁን፤ የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እረዱ፤ እና​ን​ተም ተቀ​ደሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታደ​ርጉ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ አዘ​ጋጁ።” ኢዮ​ስ​ያ​ስም ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን በዚያ ለነ​በ​ሩት ለሕ​ዝቡ ልጆች ከመ​ን​ጋው ሠላሳ ሺህ የበ​ግና የፍ​የል ጠቦ​ቶች፥ ሦስት ሺህም ወይ​ፈ​ኖች ሰጣ​ቸው፤ እነ​ዚ​ህም ከን​ጉሡ ሀብት ነበሩ። አለ​ቆ​ቹም ለሕ​ዝ​ቡና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አለ​ቆች፥ ኬል​ቅ​ያስ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ በጎ​ች​ንና ፍየ​ሎ​ችን፥ ሦስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለካ​ህ​ናቱ ሰጡ። የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች ኮኒ​ን​ያስ በን​ያ​ስም፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕ​ያ​ስና ናት​ና​ኤል፥ ሰብ​ን​ያስ፥ ኢዮ​ሄል፥ ኢዮ​ዛ​ብድ ለፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት እን​ዲ​ሆን አም​ስት ሺህ በጎ​ችን፥ አም​ስት መቶም በሬ​ዎ​ችን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ። አገ​ል​ግ​ሎ​ቱም ተዘ​ጋጀ፤ ካህ​ና​ቱም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ ቆሙ። የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ አረዱ፤ ካህ​ና​ቱም ከእ​ጃ​ቸው የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን ደም ረጩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ቍር​በ​ቱን ገፈፉ። በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ ክፍ​ላ​ቸው ለሕ​ዝቡ ልጆች እን​ዲ​ሰጡ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለዩ። እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎቹ አደ​ረጉ። የፋ​ሲ​ካ​ው​ንም በግ እንደ ሙሴ ሥር​ዐት በእ​ሳት ጠበሱ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ቍር​ባን በም​ን​ቸ​ትና በሰ​ታቴ፥ በድ​ስ​ትም ቀቀሉ፤ ተከ​ና​ወ​ነ​ላ​ቸ​ውም፤ ለሕ​ዝ​ቡም ልጆች ሁሉ በፍ​ጥ​ነት አደ​ረሱ። ከዚ​ያም በኋላ ለራ​ሳ​ቸ​ውና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ላሉ ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስቡን ለማ​ቅ​ረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ሌዋ​ው​ያን ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ አዘ​ጋጁ። የአ​ሳ​ፍም ልጆች መዘ​ም​ራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳ​ፍም፥ እንደ ኤማ​ንም የን​ጉ​ሡም ባለ ራእይ እንደ ነበ​ረው እንደ ኤዶ​ትም ትእ​ዛዝ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ነበሩ፤ በረ​ኞ​ቹም በሮ​ቹን ሁሉ ይጠ​ብቁ ነበር፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሌዋ​ው​ያን ያዘ​ጋ​ጁ​ላ​ቸው ነበ​ርና ከአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ይርቁ ዘንድ አያ​ስ​ፈ​ል​ጋ​ቸ​ውም ነበር።

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፋሲካን አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካው በግ ታረደ። ካህናቱን በየአገልግሎታቸው መደበ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎትም እንዲተጉ አበረታታቸው። እስራኤልን ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩትና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔርን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ አኑሩ፤ በእናንተ ትከሻ አትሸከሙት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። በእስራኤል ንጉሥ በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን በተጻፈው መመሪያ መሠረት፣ እንደየቤተ ሰባችሁ በክፍል በክፍላችሁ ራሳችሁን አዘጋጁ። “ሌዋውያን ባልሆኑ ወንድሞቻችሁ አንጻር እንደየቤተ ሰቡ ምድብ በተቀደሰው ስፍራ ቁሙ፤ ለእያንዳንዱም የቤተ ሰብ ምድብ ሌዋውያን ይኑሩት። ከዚያም የፋሲካውን በጎች ዕረዱ፤ ራሳችሁን ቀድሱ፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘውም መሠረት ዕርዶቹን ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።” ኢዮስያስም እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆኑ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ በግና ፍየል እንዲሁም ሦስት ሺሕ ወይፈን ከንጉሡ ሀብት ሰጠ። ሹማምቱም ለሕዝቡ፣ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ በገዛ ፈቃዳቸው አዋጥተው ሰጡ። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቆች የሆኑት ኬልቅያስ፣ ዘካርያስና ይሒኤልም ለፋሲካ መሥዋዕት የሚቀርቡ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ በግ እንዲሁም ሦስት መቶ ወይፈን ሰጡ። ደግሞም ኮናንያ፣ ወንድሞቹ ሸማያና ናትናኤል እንደዚሁም የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸቢያ፣ ይዔኤልና ዮዛባት ለፋሲካ መሥዋዕት እንዲሆኑ ዐምስት ሺሕ በግና ፍየል ዐምስት መቶም በሬ ለሌዋውያኑ ሰጧቸው። የአገልግሎቱ ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ፣ ንጉሡ ባዘዘው መሠረት ካህናቱ በየክፍላቸው ከተመደቡት ሌዋውያን ጋራ ቦታ ቦታቸውን ይዘው ቆሙ። የፋሲካው በጎች ታረዱ፤ ካህናቱ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የበጎቹን ቈዳ ገፈፉ። በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ እንደየቤተ ሰቡና እንደየምድቡ ለሕዝቡ ለመስጠት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ፤ ወይፈኖቹንም እንደዚሁ አደረጉ። እነርሱም የፋሲካውን መሥዋዕት በሥርዐቱ መሠረት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸት፣ በሰታቴና በድስት ቀቀሉ፤ ወዲያውኑም ለሕዝቡ አደሉ። ከዚህ በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ ዝግጅት አደረጉ፤ ምክንያቱም ካህናቱ የአሮን ልጆች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሥቡን እስከ ሌሊት ድረስ ያቀርቡ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ዝግጅት አደረጉ። መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር።

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢዮስያስም ለእግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ፋሲካ አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ። ካህናቱንም በየሥርዓታቸው አቆመ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ አጸናቸው። እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ተዘጋጁ፤ እንደ ሕዝቡም ልጆች እንደ ወንድሞቻችሁ በየአባቶቻችሁ ቤቶች ሆናችሁ በመቅደሱ ቁሙ፤ የሌዋውያንም ነገድ በየወገናቸው እንደ ተከፈሉ እናንተም ተከፈሉ፤ ፋሲካውንም እረዱ፤ እናንተም ተቀደሱ፤ እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ የተናገረውን ቃል ያደርጉ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።” ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም ወይፈኖች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ። መሳፍንቱም ለሕዝቡና ለካህናቱ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቆች፥ ኬልቂያስ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ። አገልግሎቱም ተዘጋጀ፤ ካህናቱም በስፍራቸው፥ ሌዋውያኑም በየክፍላቸው እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ቆሙ። ፋሲካውንም አረዱ፤ ሌዋውያኑም ቁርበቱን ገፈፉ፤ ካህናቱም ከእጃቸው የተቀበሉትን ደም ረጩ። በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ። ፋሲካውንም እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸትና በሰታቴ፥ በድስትም ቀቀሉ፤ ለሕዝቡም ልጆች ሁሉ በፍጥነት አደረሱ። ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ። የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍ፥ እንደ ኤማን፥ የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤ ካህናት የሚያከናውኑትን ተግባር መድቦ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ አበረታታቸው፤ እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም። ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ንጉሥ ሰሎሞን በሰጡአችሁ መመሪያ መሠረት በየጐሣችሁ በመመደብ በቤተ መቅደስ አገልግሎት ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤ እናንተ ሌዋውያን፥ እያንዳንዱን የእስራኤል ሕዝብ ቤተሰብ ለመርዳት እንድትችሉ እየተከፋፈላችሁ በተቀደሰው ስፍራ በቦታ በቦታቸው ራሳችሁን አደራጁ። ወገኖቻችሁ የሆኑ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ይከተሉ ዘንድ ራሳችሁን አንጽታችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።” ንጉሥ ኢዮስያስ በዚያው በፋሲካ በዓል የተገኙ ሰዎች መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቡአቸውን የራሱ ሀብት ከሆኑ የቀንድ ከብቶች፥ እንዲሁም የበግና የፍየል መንጋ፥ ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት ሺህ ወይፈኖችን ሰጠ፤ የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖችም መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ እንስሶችን በገዛ ፈቃዳቸው ለምእመናን፥ ለካህናትና ለሌዋውያን ሰጡ፤ የቤተ መቅደሱ አለቆች የሆኑት ሊቃነ ካህናቱ ሒልቂያ፥ ዘካርያስና ይሒኤልም የፋሲካ መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት መቶ በሬዎችን ለካህናት ሰጡ፤ የሌዋውያን አለቆች ኮናንያና ወንድሞቹ የሆኑ ሸማዕያና ነታንኤል እንዲሁም ሐሻብያ፥ ይዒኤልና ዮዛባድ ሌዋውያኑ ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው የሚያቀርቡአቸውን አምስት ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶችን እንዲሁም አምስት መቶ በሬዎችን ሰጡ። ለፋሲካው በዓል የሚሆነው ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ፥ ካህናቱ በስፍራቸውና ሌዋውያኑም በየክፍላቸው በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ቦታ ቦታቸውን ያዙ፤ ለፋሲካውም በዓል የታረዱትን የበግና የፍየል ጠቦቶች ሌዋውያኑ ቆዳቸውን ገፈፉአቸው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡትን እንስሶች በየቤተሰቡ ለተመደበው ሕዝብ አከፋፈሉ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት በኦሪት ሕግ በተሰጠው መመሪያ መሠረት መሥዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ ነው፤ እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ፤ ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት የፋሲካውን መሥዋዕት በእሳት ጠበሱት፤ የተቀደሰውንም ቊርባን በምንቸት፥ በሰታቴና በድስት ቀቅለው ሥጋውን በፍጥነት ለሕዝቡ አከፋፈሉ፤ ከዚህም በኋላ ሌዋውያኑ ለራሳቸውና የአሮን ዘሮች ለሆኑት ካህናት የፋሲካን መሥዋዕት አዘጋጁ፤ ይህንንም ያደረጉት ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን በሙሉ ለማቃጠል እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ስለ ነበር ነው፤ ከዚህ በታች ስማቸው የተመለከተው የሌዋዊው የአሳፍ ጐሣ የሆኑ መዘምራንም ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፥ በተመደበላቸው ስፍራ ነበሩ፤ እነርሱም አሳፍ፥ ሄማንና የንጉሡ ነቢይ ይዱታን ናቸው፤ ሌሎች ሌዋውያን የፋሲካውን መሥዋዕት ያዘጋጁላቸው ስለ ነበር፥ የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች ስፍራቸውን አይተዉም ነበር፤

2 ዜና መዋዕል 35:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢዮስያስም ለጌታ በኢየሩሳሌም ፋሲካን አከበረ፤ በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን መሥዋዕት አረዱ። ካህናቱንም በየሥርዓታቸው አቆመ፥ በጌታም ቤት እንዲያገለግሉ አጸናቸው። እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለጌታም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ “ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ራሳችሁን አዘጋጁ፤ እንደ ሕዝቡም እንደ ወንድሞቻችሁ በየአባቶቻችሁ ቤቶች ሆናችሁ በመቅደሱ ቁሙ፤ ለእያንዳንዱ ለተከፋፈሉትም ለአባቶች ቤቶች ሌዋውያን ይኑሯቸው፤ ፋሲካውንም እረዱ፥ እናንተም ተቀደሱ፥ ጌታም በሙሴ አንደበት የተናገረውን ቃል እንዲያደርጉ ለወንድሞቻችሁ አዘጋጁ።” ኢዮስያስም ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን በዚያ ለነበሩት ለሕዝቡ ልጆች ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች፥ ሦስት ሺህም በሬዎች ሰጣቸው፤ እነዚህም ከንጉሡ ሀብት ነበሩ። መሳፍንቱም ለሕዝቡና ለካህናቱ ለሌዋውያኑም በፈቃዳቸው ሰጡ፤ የጌታም ቤት አለቆች፥ ኬልቂያስ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ በጎችና ፍየሎች፥ ሦስት መቶም በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። የሌዋውያኑም አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤል፥ ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን አምስት ሺህ በጎችና ፍየሎች፥ አምስት መቶም በሬዎች ለሌዋውያን ሰጡ። አገልግሎቱም በተዘጋጀ ጊዜ ካህናቱም በስፍራቸው፥ ሌዋውያኑም በየክፍላቸው እንደ ንጉሡ ትእዛዝ ቆሙ። የፋሲካውንም መሥዋዕት አረዱ፥ ሌዋውያኑም ቁርበቱን ገፈፉ፥ ካህናቱም ከእጃቸው የተቀበሉትን ደም ረጩ። በሙሴም መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ለጌታ እንዲያቀርቡ በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሕዝቡ ልጆች እንዲሰጡ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለዩ። እንዲሁም በበሬዎቹ አደረጉ። የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ። ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ። የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።