YouVersion Logo
Search Icon

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

DAY 21 OF 28

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ደስታ በኢየሱስ የህይወትና የፍቅር ኅይል ላይ ያነጣጠረ የእምነትና የተስፋ ጥልቅ ውሳኔ ነው።
የኢየሱስ ፍቅር ሞትን ሳይቀር እንዳሸነፈ ሲያምኑ፣ በሚያስገርም ሁኔታ ደስታ ጭልም ባሉ ሁኔታዎች ሳይቀር ባልተለመደ መልኩ ምክንያታዊ ይሆናል። ይህ ሀዘንን ችላ ማለት ወይም ማመቅ አለብዎ ማለት አይደለም። ይህ ጤናማ ወይም አስፈላጊ አይደለም። ጳውሎስ የሚወዳቸውን ሰዎች ወይም ነጻነቱን ሲናፍቅ ሀዘኑን ይገልጥ ነበር። ሀዘንተኛ ሆኖ ደስተኛ መሆን ብሎ ይጠራዋል። ለሕመሙ እውቅና እየሰጠ፣ ደግሞም ጉዳቱ የዘላለም እንደማይሆን ለማመን ጌታን መታመን መረጠ።

ያንብቡ፦

2ኛ ቆሮንቶስ 6÷10

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

በህይወትዎ ሀዘን ተሞልተው እያሉ ነገር ግን በሙላት ሀሴት ያደረጉበትን ወቅት ማስታወስ ይችላሉ ? ከሆነ፣ ያንን ተሞክሮ እንዴት ይገልጹታል?

አሁን ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ። እጅግ ታላቅ የሆነን መከራ አልፎ ስለሚጸናው ደስታው እግዚአብሔርን አመስግኑ። በመከራ መካከል ደስ መሰኘትን እንዲያስተምርዎ እግዚአብሔርን ይጠይቁ። ግልጽ ሆነው የሚያታግልዎትን ነገር ለእርሱ ይንገሩና የሚያስፈልግዎትን ነገር ይጠይቁት።

Day 20Day 22

About this Plan

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More