BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችSample
ኢየሱስ ተከታዮቹን እንዲህ ሲል አስተማረ "ሰዎች እኔን በመከተላችሁ ምክንያት ባይቀበሏችሁ ወይም ቢያሳድዷችሁ፣ ሀሴት አድርጉ፣ በጣምም ደስ ይበላችሁ፣ ምክንያቱም ዋጋችሁ በሰማይ እጅግ ታላቅ ነው።" በኢየሱስ ትምህርት ውስጥ የምናየው እውነተኛ ደስታ በሁኔታዎች ላይ ስላልተመሰረተ እጅግ አስከፊ የሚባልን ሁኔታ ሳይቀር ይቋቋማል። ይልቁንም ደስታ የሚመረኮዘው በእግዚአብሔር እና እግዚአብሔር ለህዝቡ ስለወደፊት ዕጣ-ፈንታቸው በገባው የተስፋ ቃል ላይ ነው።
ያንብቡ፦
ማቴዎስ 5÷11-12፣ የሐዋሪያት ሥራ 13÷50-52፣ ዕብራውያን 12÷1-3
ምልከታዎን ያስፍሩ፡
በእነዚህ ክፍሎች መሰረት፣ በሚያሙና በሚያሰጉ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ደስታን እንዴት ማቆየት ይቻላል?
ዕብራውያን 12÷1-3ን በመከለስ ትንሽ ጊዜ ያሳልፉ። ኢየሱስ በታላቅ መከራ መጽናት የቻለው ከመከራው ባሻገር በፊቱ ያለውን ታላቅ ደስታ መመልከት ስለቻለ ነው። በዚህ ክፍል የኢየሱስ ተከታዮች ኢየሱስን በመመልከት በመከራ እንዲጸኑ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፤ እርሱ በፊታቸው ያለ ደስታ ይሆንላቸዋል። "እየታን በኢየሱስ ላይ ማድረግ" በተግባር ምን ሊመስል ይችላል ብለው ያስባሉ?
ምልከታዎን ከልብዎ የመነጨ ጸሎት አድርገው ለእግዚአብሔር አቅርቡት።
About this Plan
ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።
More